አዲስ ጊዜ

230 Posts
አስፋውን ተሰናበትነው  

አስፋውን ተሰናበትነው  

በበርካቶች ዘንድ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ "ሞቅ ደመቅ ሸብረቅ" በምትል ንግግሩ ይታወቃል፡፡ አስፋው መሸሻ፡፡ መሸሻ ይሙት የሚለው መሃላውም አይረሳም፡፡ ከአባቱ ከአቶ መሸሻ አስፋው እና ከእናቱ ከ ወ/ሮ ዘነበወርቅ አሻግሬ ሀምሌ 1959 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ‹‹ሰሜን ማዘጋጃ  ችሎት ሰፈር››  በሚባለው አካባቢ የተወለደው አስፋው ለቤተሰቡ አምስተኛ ልጅ እንደሆነ ይነገራል።አባቱ ዲፕሎማት በመሆናቸው እና ለሥራ ጉዳይ ወደ ተለያዩ ክፍለ ዓለማት ይዘዋወሩ ስለነበር ትምህርቱን በኢትዮጵያ፣ታንዛንያ እና ኬንያ ተከታትሏል። አስፋው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ  ከጓደኛው ዳንኤል ግዛው ጋር በኤፍ ኤም 97.1 ላይ በጋራ  "አይሬ"የተሰኘ ፕሮግራም ማዘጋጀት እና ማቅረብ ጀመረ፡፡ በአይሬ ፕሮግራሙ ተወዳጅነትን ያተረፈው አስፋው ከሃገር እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በኤፍ ኤም 97.1…
ተጨማሪ ያንብቡ
 1 ነጥብ 7 ትሪሊየን ብር በቴሌብር ብቻ ማንቀሳቀስ ተችሏል -ኢትዮ ቴሌኮም

 1 ነጥብ 7 ትሪሊየን ብር በቴሌብር ብቻ ማንቀሳቀስ ተችሏል -ኢትዮ ቴሌኮም

14/06/2016 የቴሌ ብር አገልግሎት ከተጀመረ በኋላ በአጠቃላይ የግብይት መጠን 1 ነጥብ 7 ትሪልየን ብር በኢኮኖሚው ላይ ማንቀሳቀሱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም ይኼን የገለጸው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ስራ አፈጻጸሙን በዛሬው ዕለት ጥር 14 2016 በስካይ ላይት ሆቴል ባሳወቀበት መድረክ ነው። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴሌ ብር አገልግሎት ከ41 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራቱንም ተናግረዋል፡፡እንዲሁም በቴሌብር ሳንዱቅ፣ ቴሌ ብር እንደኪሴ፣ ቴሌብር መላ እና ሌሎችም የፉይናንስ አገልግሎት 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ደንበኞችን አፍርቶ፤ 8 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የብድር አገልግሎት እንዲሁም በቁጠባ አገልግሎት 8 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መቀመጡ ታውቋል። በተጨማሪም ከዲጂታል…
ተጨማሪ ያንብቡ
አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የሀገራችንን ስፖርታዊ እና ታሪካዊ  ክንውኖችን በማቅረብ  በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ የሚመሰክሩለት አንጋፋው ጋዜጤኛ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ ዛሬ አርፏል፡፡ ገነነ የተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች በመስራት፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ  በማቅረብ  በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል። ለአብነት በቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ በኤፍ ኤም አዲስ ፣ በብስራት ኤፍ ኤም ፣ በአሻም ቴሌቪዥን ላይ የተለያዩ የታሪክና የስፖርት ዝግጅቶችን ባማረና ቀልብን በሚስብ አቀራረብ ሰርቷል። የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ባለው አስተዋጽኦ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎልደን ኦፍ ሜሪት ሽልማትም ሸልሞታል። ስድስት ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው።  መጋቢት 5/1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ ፤ ስፖርትና…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ለይፋዊ ጉብኝት ትናንት ኳታር ገብተዋል።

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ለይፋዊ ጉብኝት ትናንት ኳታር ገብተዋል።

14/05/2016 ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ወደ ዶሃ የተጓዙት፣ በቅርብ ጊዜያት በሱማሊያ በተፈጠሩ እንዳንድ ክስተቶች ዙሪያ ከአገሪቱ መሪዎች ጋር ለመወያየት እንደኾነ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ በሱማሊያና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት ከተፈጠረ ወዲህ፣ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ በኤርትራና ግብጽ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። ሶማሊላንድ ግን ከኢትዮጵያ ጋር ከተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ማናቸውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደምትቃወም አስታውቃለች። ሶማሊላንድ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴሯ በኩል ትናንት ባወጣችው መግለጫ፣ ግብጽ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን እንደ ሱዳን፣ ሊቢያና ጋዛ በመሳሰሉ ግጭቶች ባሉባቸው ጎረቤቶቿ ላይ ብታውለው ይሻላታል ብላለች። ቀጠናዊ ጉዳዮችን በንግግርና ትብብር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኗን የጠቀሰችው ሶማሊላንድ፣ በቀጠናው ሰላምና…
ተጨማሪ ያንብቡ
 በትግራይክልል  28% ህፃናት የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

 በትግራይክልል  28% ህፃናት የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

አሸናፊ አሰበ 14/06/2016 በትግራይ ክልል ከተከሰተው አስከፊ ድርቅ ጋር ተያይዞ   ህፃናት በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጥረት እየተጎዱ ነው የክልሉ ጤና ቢሮ ከ ትግራይ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጋር በመተባበር በጋራ አካሄድኩት ባላው ጥናት 26% የክልሉ ህጻናት መካከለኛ እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው መረጋገጡን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የ ስነ-አመጋገብ ጉዳይ ቡድን አስተባባሪ አቶ መንገሻ ባህረሥላሴ ለ አዲስ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ እንደ ሃላፊው ገለጻ ጥናቱ የተካሄደው በትግራይ ክልል ውስጥ ካሉ ወረዳዎች ውስጥ በ 36 ቱ ብቻ ሲሆን በምግብ እጥረት ምክንያት በሆስፒታሎች ውስጥ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንም አክለዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሚያስተዳድራቸው 73 ወረዳዎች ውስጥ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የሚገኘው ድጋፍ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ አብነት ታምራት መታሰሩ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ አብነት ታምራት መታሰሩ ተሰምቷል።

14/06/2016 ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ በበርካታ ጋዜጣና መጽሔቶች በአዘጋጅነት ሲሰራ የቆየው ጋዜጠኛ አብነት ታምራት፣ የከተራ ዕለት በመንግስት የደህንነቶች ኃይሎች መያዙ ተሰምቷል። አብነት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥሮ መያዙ የተሰማ ሲሆን ትላንትና ሰኞ ፍርድ ቤት አለመቅረቡን እና ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱ ታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
“በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር የሚያሳየው፣ የሀገሪቱ ሁኔታ ለመገናኛ ብዙሃን አመቺ አለመሆኑን ነው”ሲፒጄ

“በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር የሚያሳየው፣ የሀገሪቱ ሁኔታ ለመገናኛ ብዙሃን አመቺ አለመሆኑን ነው”ሲፒጄ

12/06/2016 ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሃገራት ሶስተኛ ደረጃ መያዟን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል። በአፍሪካ በታሳሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ኤርትራ ቀዳሚ ስትሆን ግብፅ ሁለተኛዋ ሃገር ሁናለች፡፡ ሲፒጄ ዓመታዊ ሪፖርቱን ባጠናቀረበት ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ገደማ፤ በመላው ዓለም የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት 320 እንደነበር ገልጿል።ከእነዚህም መሃል 5ቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ ይህ ቁጥር ድርጅቱ መሰል ሪፖርቶች ማዘጋጀት ከጀመረበት ከ1985 ዓ.ም. ወዲህ በከፍተኛነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ መሆኑንም ጠቁሟል። በአፍሪካ እስካለፈው ህዳር መጨረሻ ድረስ ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፤ ቢያንስ 67 የሚሆኑ ጋዜጠኞች “ከስራቸው ጋር በተያይዘ ለእስር መዳረጋቸውን” ሲፒጄ በሪፖርቱ አመልክቷል።…
ተጨማሪ ያንብቡ
”የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛትን የሚመለከት ማንኛውም ስምምነት የሃገሪቱን መንግስት ይሁንታ ሊያገኝ ይገባል” ኢጋድ

”የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛትን የሚመለከት ማንኛውም ስምምነት የሃገሪቱን መንግስት ይሁንታ ሊያገኝ ይገባል” ኢጋድ

በእታገኘሁ መኮነን 09/05/2016 የቀጠናው ሃገራት እና የቀጠናውን ጉዳይ በትኩረት የሚከታተሉ ሁሉ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ሐሙስ ጥር 9፤ 2016 በኡጋንዳ ኢንተቤ ከተማ ተካሂዷል፡፡ መሪዎቹ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ባወጡት መግለጫ ''የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛትን የሚመለከት ማንኛውም ስምምነት የሀገሪቱን መንግስት ይሁንታ ሊያገኝ ይገባል ''  ብለዋል ፡፡መሪዎቹ ማንኛውም ግንኙነት የሶማሊያን ''ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ያከበረ ሊሆን እንደሚገባም'' አሳስበዋል። በጉባኤው ላይ የአስተናጋጇ ሀገር ኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፣  የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ፣የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ አደጋ አጋጠመው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ አደጋ አጋጠመው

09/05/2016 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን፤ ዛሬ ሐሙስ በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራትቶ መውጣቱን  ሆኖም በአደጋው በመንገደኞችም ላይ ሆነ የበረራ ሰራተኞች  ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ  አየር መንገዱ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአውሮፕላኑ ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡ ጉዳት የደረሰበት የአየር መንገዱ አውሮፕላን  የበረራ ቁጥር ኢቲ 106 ሲሆን ፤ ከአዲስ አበባ የተነሳው ከቀኑ 6፡30 እደሆነ ታውቋል። ክስተቱ የደረሰው ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከአስ8፡10  ደቂቃ ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል። አየር መንገዱ  ለተፈጠረው ችግር ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቆ “የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ” ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡

09/05/2016 የአረብ ሊግ በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልፅ የጣሰ ነው፤  ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚፃረር ነው በሚል ተቃውሟል። የአረብ አፍሪካና የዓለም አቀፍ መርሆች ላይ በግልፅ የተሰነዘረ ጥቃት ነውም ብሏል። የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሊጉ መግለጫ፥ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለውታል፡፡ አክለው  ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት ሆኖም የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ ነው ብለዋል፡፡ የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ ባካሄደው የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ በኢትዮጵያና…
ተጨማሪ ያንብቡ