09/05/2016
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን፤ ዛሬ ሐሙስ በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራትቶ መውጣቱን ሆኖም በአደጋው በመንገደኞችም ላይ ሆነ የበረራ ሰራተኞች ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ አየር መንገዱ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአውሮፕላኑ ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡
ጉዳት የደረሰበት የአየር መንገዱ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 106 ሲሆን ፤ ከአዲስ አበባ የተነሳው ከቀኑ 6፡30 እደሆነ ታውቋል። ክስተቱ የደረሰው ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከአስ8፡10 ደቂቃ ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው ችግር ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቆ “የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ” ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡
