አሸናፊ አሰበ
14/06/2016
በትግራይ ክልል ከተከሰተው አስከፊ ድርቅ ጋር ተያይዞ ህፃናት በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጥረት እየተጎዱ ነው
የክልሉ ጤና ቢሮ ከ ትግራይ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጋር በመተባበር በጋራ አካሄድኩት ባላው ጥናት 26% የክልሉ ህጻናት መካከለኛ እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው መረጋገጡን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የ ስነ-አመጋገብ ጉዳይ ቡድን አስተባባሪ አቶ መንገሻ ባህረሥላሴ ለ አዲስ ጊዜ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሃላፊው ገለጻ ጥናቱ የተካሄደው በትግራይ ክልል ውስጥ ካሉ ወረዳዎች ውስጥ በ 36 ቱ ብቻ ሲሆን በምግብ እጥረት ምክንያት በሆስፒታሎች ውስጥ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንም አክለዋል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሚያስተዳድራቸው 73 ወረዳዎች ውስጥ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የሚገኘው ድጋፍ እየተከፋፈለ ያለው ለ 20 ወረዳዎች ብቻ ነው ያሉት አቶ መንገሻ ተጎጂ ለሆነው ሁሉ ድጋፉን ማድረስ ባለመቻሉ ችግሩ እየተባባሰ ነው ብለዋል፡፡
በምግብ እጥረት ምክንያት እያጋጠመ ያለ ሞት እየጨመረ ነው ያሉት አቶ መንገሻ ጡት በሚያጠቡ እናቶች ላይ የሚታየው የምግብ እጥረት ደግሞ በጣም የሚያሳስብ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ አስተያየታቸው ሰጥተውናል፡፡
እንደ አጠቃላይ የምግብ እጥረት ያለባቸው ህፃናትን ለመታደግ አሁንም የእርዳታ እጥረት እንደሚታይ አቶ መንገሻ ለአዲስ ጊዜ ነግረዋታል።
