የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በ100 ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ::
27/06/2016 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ 100 ሺህ ብር የዋስትና ገንዝብ በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ በፍርድ ቤት ተወሰነላቸው። “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት 13 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት አቶ በቴ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ በዛሬው ችሎት ላይ ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም” በሚል ተጨማሪ 11 የምርመራ ቀናትን ጠይቋል።የአቶ በቴን የስልክ የምርመራ ውጤት ለመቀበል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በተደጋጋሚ ጥያቄ ባቀርብም እስካሁን ውጤቱን ለመቀበል አልቻልኩም ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልጓቸው አስረድተዋል። የአቶ በቴ ጠበቃ አቶ ቦና ያዘው፤ በተጠርጣሪው ስልክ ላይ “ምርመራ…