የጋዜጠኛዉ ድምፅ

“የሚዲያ አዋጅ ማሻሻያ ” ወደፊት ወይስ ወደኋላ ?

እታገኘሁ መኮነን የ2010ሩ ለውጥ እና የሚዲያው መነቃቃት 2010 ዓ.ም  ፤የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የሃገር ግንባታ ሂደት ላይ ከታዩት ለውጦች  መሃል አንዱ ለሚዲያው አንጻራዊ የሚባል ነጻ የመጫወቻ ሜዳ መፍቀድ ነበር ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም  2013 ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፀደቀ ፤የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013፡፡ ይሄ አዋጅ ከዛ ቀደም ብሎ...

በአተገባበሩ ላይ ተቃውሞ ይቀርብበት የነበረውን የሚዲያ አዋጅ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞ ቀረበ፡፡

ረቂቅ አዋጁን በመቃወም 14 የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ እታገኘሁ መኮነን ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቅምት 19ቀን2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ...

ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

እታገኘሁ መኮነን MELA ( Media Lawyers alliance )ተብሎ የተሰየመው ይህ የሚዲያ እና የህግ ባለሞያዎች ጥምረት በምስረታ ሂደት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ) ሰምተናል፡፡ ኅብረቱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በመሆን  በጥምረቱ ዙሪያ  ትናንት ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ)...

 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

ማህበሩ የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደትም ከፖለቲካ አተያይ በፀዳ መንገድ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አዲስ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በአዲስ አበባ ቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን መጎብኘታቸውን ትናንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ስለ ማረሚያ ቤት አያያዝ እና አጠቃላይ የፍትህ ሂደቱ ያለበትን ሁኔታ ከጋዜጠኞቹ ጋር እንደተወያዩ ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ በእስር ላይ...

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ። ዛሬ እና ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።  በትናንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት ሶስቱ ጋዜጠኞች የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” ማድረጉን በመጥቀስ ለፍርድ ቤት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት ነበር። ከአቤቱታ አቅራቢዎች አንዱ...

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋዜማ ሬዲዮ፣ ኢኤምኤስ እና ሌሎችም ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ግንባታ” ናቸው ተብለው በፈረሱ ወደ 100 ሺህ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችና በተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ለዘገባ ወደ ስፍራው ባመራበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ለእስር ተዳርጎም ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በፖሊስ ድብደባ፣ እስርና ማዋከብ ደርሶበት እንደነበር የተናገረው ጋዜጠኛ ሳሙኤል...

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

የቴሌቪዥን ባለንብረቶች ለሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል አሉ፡፡ በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የሚከለው ዋጋ ውድነት አሳስቧት ነበር አባላቱ ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም ለእነዚህ የቴሌቭዥን ባለንብረቶች  ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል ብሎ ማበረታቻ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ...

አውሮፓዊያን እና አሜሪካ ተባብረው እያስፈራሩኝ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች፡፡

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ 18 ምዕራባውያን ሀገራት  እና ኢምቢሲዎች እና የአሜሪካ ኤምባሲ ‘የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን’ አስመልክተው ባሳለፍነው ሳምንት ባወጡት የጋራ መግለጫ የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች አያያዝ መተቸታቸው ይታወሳል፡፡ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ቤልጂየም፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ኔዘርላንድ እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ  ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንድታከብር ጠይቀዋል፡፡ ሀገራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ...

የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የፖለቲካ ውጥረት በተፈጠረ ቁጥር ጋዜጠኞችን ማሠር እንዲያቆሙ  ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ድርጅቱ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጸጥታ ኃይሎች ስምንት ጋዜጠኞችን እንዳሠሩ ገልጦ፣ እስር ቤት በሚገኙ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ ደሞ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ብሏል። የበይነ መረብ ጋዜጠኞቹ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና ከሁለት ወራት በፊት የታሠረው የሱማሌ ክልሉ ጋዜጠኛ...