የጋዜጠኛዉ ድምፅ

“የሚዲያ አዋጅ ማሻሻያ ” ወደፊት ወይስ ወደኋላ ?

“የሚዲያ አዋጅ ማሻሻያ ” ወደፊት ወይስ ወደኋላ ?

እታገኘሁ መኮነን የ2010ሩ ለውጥ እና የሚዲያው መነቃቃት 2010 ዓ.ም  ፤የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የሃገር ግንባታ ሂደት ላይ ከታዩት ለውጦች  መሃል አንዱ ለሚዲያው አንጻራዊ የሚባል ነጻ የመጫወቻ ሜዳ መፍቀድ ነበር ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም  2013 ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፀደቀ ፤የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013፡፡ ይሄ አዋጅ ከዛ ቀደም ብሎ ለ10 ዓመታት ያህል የሰራበትን የጋዜጠኝነት ሙያ በአፈና፣ በነጻነት ሃሳብን እና እውነትን መዘገብን በመነፈግ፣ በጫና እና ባለመመቸት ምክንያት ጥሎ ለመውጣት ለተገደደው ጋዜጠኛ ካህሳይ ብሩ እና የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም ለመላው የሚዲያ ማህበረሰብ ፤ከዚያም ከፍ ሲል ደግሞ ሃሳብን በነፃነት በመግለፅ ለሚያምኑ ለዚህም ለሚተጉ የሰብዓዊ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በአተገባበሩ ላይ ተቃውሞ ይቀርብበት የነበረውን የሚዲያ አዋጅ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞ ቀረበ፡፡

በአተገባበሩ ላይ ተቃውሞ ይቀርብበት የነበረውን የሚዲያ አዋጅ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞ ቀረበ፡፡

ረቂቅ አዋጁን በመቃወም 14 የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ እታገኘሁ መኮነን ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቅምት 19ቀን2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ 14  የጋዜጠኝነት የሙያ ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቾች የአዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይትም ባልተካሔደበት ሁኔታ ረቂቁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡ፣ እንዲሁም በአዋጁ ከለላ ተሰጥቷቸው የነበሩ የቁጥጥርና…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

እታገኘሁ መኮነን MELA ( Media Lawyers alliance )ተብሎ የተሰየመው ይህ የሚዲያ እና የህግ ባለሞያዎች ጥምረት በምስረታ ሂደት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ) ሰምተናል፡፡ ኅብረቱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በመሆን  በጥምረቱ ዙሪያ  ትናንት ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ)  ዳሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ ጥምረቱ  የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራትን ማገዝ፣ጋዜጠኞች በሰሩት ስራ ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት እና ጫና የሕግ ድጋፍ የመሰጠት፣ለጋዜጠኞች መታሰር ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር የማድረግ፣ በመገናኛ ብዙኃን ዙሪያ  ህጎች ሲወጡ በባለሞያዎች ጥናት ማስጠናት እና ግብዓት ማቅረብ እንዲሁም በሚዲያው ህብረተሰብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

ማህበሩ የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደትም ከፖለቲካ አተያይ በፀዳ መንገድ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አዲስ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በአዲስ አበባ ቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን መጎብኘታቸውን ትናንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ስለ ማረሚያ ቤት አያያዝ እና አጠቃላይ የፍትህ ሂደቱ ያለበትን ሁኔታ ከጋዜጠኞቹ ጋር እንደተወያዩ ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር በተያዙበት ወቅት የተያዙበት መንገድም ሆነ ከተያዙ በኃላ ያለው የፍርድ ቤት ሂደት አግባብነት እንደሚጎድለው ተናግረዋል፡፡ በሁለቱም ማረሚያ ቤቶች ከሁለት ዓመት በላይ ሳይፈረድባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞች መኖራቸውን ማኅበሩ እንዳረጋገጠ አስታውቋል። ስለሆነም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የሚዲያ ምህዳሩ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ። ዛሬ እና ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።  በትናንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት ሶስቱ ጋዜጠኞች የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” ማድረጉን በመጥቀስ ለፍርድ ቤት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት ነበር። ከአቤቱታ አቅራቢዎች አንዱ የሆነው የ“ኢትዮ ኒውስ”  የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ ሰኞ ሰኔ 10፤ 2016 የተፈታ ሲሆን አስር ወራትን በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ያሳለፈው ሌላኛው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ፤ ባለፈው አርብ ሰኔ 7፤ 2016 ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋዜማ ሬዲዮ፣ ኢኤምኤስ እና ሌሎችም ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ግንባታ” ናቸው ተብለው በፈረሱ ወደ 100 ሺህ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችና በተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ለዘገባ ወደ ስፍራው ባመራበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ለእስር ተዳርጎም ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በፖሊስ ድብደባ፣ እስርና ማዋከብ ደርሶበት እንደነበር የተናገረው ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋስ ከእስር ቤት ወጥቶ እንዲከራከር በፍርድ ቤት ተወስኖለት ቢወጣም ዛቻና ማስፈራሪ ሲደርስበት እንደነበረ ነግሮኛል ሲል ኢትዮ ነጋሪ አስነብቧል፡፡ በቅርቡም ለዋዜማ ሬድዮ እና ኢንተር ኒውስ ዘገባ ለመስራት ወደ አማራ ክልል ደሴና ሐይቅ ከተሞች በተጓዘበት ወቅት በክልሉ ኮማንድ ፖስት ታስሮ እንደነበረም አክሏል።…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

የቴሌቪዥን ባለንብረቶች ለሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል አሉ፡፡ በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የሚከለው ዋጋ ውድነት አሳስቧት ነበር አባላቱ ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም ለእነዚህ የቴሌቭዥን ባለንብረቶች  ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል ብሎ ማበረታቻ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ ሰባ የሚሆኑ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች  ስርጭታቸውን በኢትዮሳት በኩል ያደረጉ ሲሆን ዓመታዊ ወጪያቸው ግን እንዳልቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ብሮድካስተሮች ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ወጪ ለመቀነስ ብለው ወደ ኢትዮሳት የገቡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዓመት ለሳተላይት ስርጭት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
አውሮፓዊያን እና አሜሪካ ተባብረው እያስፈራሩኝ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች፡፡

አውሮፓዊያን እና አሜሪካ ተባብረው እያስፈራሩኝ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች፡፡

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ 18 ምዕራባውያን ሀገራት  እና ኢምቢሲዎች እና የአሜሪካ ኤምባሲ ‘የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን’ አስመልክተው ባሳለፍነው ሳምንት ባወጡት የጋራ መግለጫ የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች አያያዝ መተቸታቸው ይታወሳል፡፡ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ቤልጂየም፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ኔዘርላንድ እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ  ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንድታከብር ጠይቀዋል፡፡ ሀገራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው “ማስፈራሪያ እና እስር ይደርሰባቸዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰውም ነበር። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ በዚህ ዙሪያ ለጋዜጠኞች  በሰጡት መግለጫ  ምዕራባዊን ሀገራት በቡድን መግለጫ በማውጣት  ሊያስፈራሩን ሞክረዋል   ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ኢትዮጵያ መግለጫውን ካወጡት እያንዳንዳቸው ሀገራት ጋር…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የፖለቲካ ውጥረት በተፈጠረ ቁጥር ጋዜጠኞችን ማሠር እንዲያቆሙ  ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ድርጅቱ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጸጥታ ኃይሎች ስምንት ጋዜጠኞችን እንዳሠሩ ገልጦ፣ እስር ቤት በሚገኙ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ ደሞ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ብሏል። የበይነ መረብ ጋዜጠኞቹ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና ከሁለት ወራት በፊት የታሠረው የሱማሌ ክልሉ ጋዜጠኛ ሙሂያዲን ሞሃመድ ባስቸኳይ እንዲፈቱና በገነት ላይ ተፈጽሟል የተባለው ጥቃትም እንዲጣራ ሲፒጄ ጠይቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
አስፋውን ተሰናበትነው  

አስፋውን ተሰናበትነው  

በበርካቶች ዘንድ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ "ሞቅ ደመቅ ሸብረቅ" በምትል ንግግሩ ይታወቃል፡፡ አስፋው መሸሻ፡፡ መሸሻ ይሙት የሚለው መሃላውም አይረሳም፡፡ ከአባቱ ከአቶ መሸሻ አስፋው እና ከእናቱ ከ ወ/ሮ ዘነበወርቅ አሻግሬ ሀምሌ 1959 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ‹‹ሰሜን ማዘጋጃ  ችሎት ሰፈር››  በሚባለው አካባቢ የተወለደው አስፋው ለቤተሰቡ አምስተኛ ልጅ እንደሆነ ይነገራል።አባቱ ዲፕሎማት በመሆናቸው እና ለሥራ ጉዳይ ወደ ተለያዩ ክፍለ ዓለማት ይዘዋወሩ ስለነበር ትምህርቱን በኢትዮጵያ፣ታንዛንያ እና ኬንያ ተከታትሏል። አስፋው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ  ከጓደኛው ዳንኤል ግዛው ጋር በኤፍ ኤም 97.1 ላይ በጋራ  "አይሬ"የተሰኘ ፕሮግራም ማዘጋጀት እና ማቅረብ ጀመረ፡፡ በአይሬ ፕሮግራሙ ተወዳጅነትን ያተረፈው አስፋው ከሃገር እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በኤፍ ኤም 97.1…
ተጨማሪ ያንብቡ