የወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ የት ደረሰ ?
የፌደራል ዋና ኦዲተር የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ተቋማትን የበጀት ኦዲት ዋና ዋና ግኝቶችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ዋና ኦዲተር በሪፖርቱ ላይ እንዳለው ከህዝብ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ኦዲት ካደረጋቸው ስራዎች መካከል የወሎ ተርሸሪ የህክምና እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ዋነኛው ነው፡፡ በተሰራው የኦዲት ሪፖረት መሰረትም ለሆስፒታሉ ግንባታ በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ በሀገር ውስጥ እና ውጭ ሀገራት ሲደረግ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ለዚህም ሲባል በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች፣ ክልሎች እና ሌሎች አካባቢዎች ይሸጣል ተብሎ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ኩፖን ተሰራጭቶ እንደነበር በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ይሁንና ይህ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው የገቢ መሰብሰቢያ…
