ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው ባወጣው መግለጫው ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት አስታውቋል። መግለጫው የወጣው በትናንትናው እለት የግብፅ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ቀሳቁስ እና ወታደሮችን ማጓጓዛቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ነው። "ኢትዮጵያ ብሄራዊ ፀጥታዋን ሊያውኩ የሚችሉ በቀጠናው እየተከናወኑ ያሉ ድርጊቶችን በንቃት እየተከታተለች ነው" ያለው መግለጫው የሶማልያ መንግስት ከውጫዊ ሀይሎች ጋር በማበር ቀጠናው ላይ ውጥረት እየፈጠረ ነው ብሎ ከሷል። መግለጫው አክሎም "ለአጭር ግዜ እና እርባና ቢስ ጥቅም ብለው አካባቢው ላይ ውጥረት የሚነዙ ሀይሎች ለድርጊታቸው ተጠያቂ ይሆናሉ" ብሏል። ይሁንና መግለጫው በትናንትናው እለት አውሮፕላኖችን ወደ ሶማልያ ያሰማራችውን ግብፅን በስም አልጠቀሰም። የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና…
