አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የሀገራችንን ስፖርታዊ እና ታሪካዊ  ክንውኖችን በማቅረብ  በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ የሚመሰክሩለት አንጋፋው ጋዜጤኛ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ ዛሬ አርፏል፡፡

ገነነ የተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች በመስራት፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ  በማቅረብ  በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል።

ለአብነት በቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ በኤፍ ኤም አዲስ ፣ በብስራት ኤፍ ኤም ፣ በአሻም ቴሌቪዥን ላይ የተለያዩ የታሪክና የስፖርት ዝግጅቶችን ባማረና ቀልብን በሚስብ አቀራረብ ሰርቷል።

የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ባለው አስተዋጽኦ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎልደን ኦፍ ሜሪት ሽልማትም ሸልሞታል። ስድስት ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው። 

መጋቢት 5/1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ ፤ ስፖርትና ታሪክ አጣምሮ የሚወድ ፣ ለሚናገራቸውም ወይም ለሚያቀርባቸው የጽሁፍ ስራዎች በቂ ማስረጃ እና ሰነድ ይዞ የሚቀርብ በመሆኑ  ” ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሐፍት ” የሚል ስያሜንም አግኝቷል።

ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ዛሬ ህይወቱ አልፏል።