የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው ባወጣው መግለጫው ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት አስታውቋል። መግለጫው የወጣው በትናንትናው እለት የግብፅ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ቀሳቁስ እና ወታደሮችን ማጓጓዛቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ነው። “ኢትዮጵያ ብሄራዊ ፀጥታዋን ሊያውኩ የሚችሉ በቀጠናው እየተከናወኑ ያሉ ድርጊቶችን በንቃት እየተከታተለች ነው” ያለው መግለጫው የሶማልያ መንግስት ከውጫዊ ሀይሎች ጋር...
ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ኢትዮጵያ ከስድስት ወራት በፊት የባህር በር መግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ነበር ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ ውስጥ የገቡት፡፡ በዚህም ምክንያት ሰኔ 24/ 2016 ዓ.ም በቱርክ ጋባዥነት ለመጀመሪያ ጊዜ በመሃላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ ለመነጋገር ወደ ቱርክ አንካራ ያቀኑት ኢትዮጵያና ሶማሊያ በመካከላቸው ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ...
14/05/2016 ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ወደ ዶሃ የተጓዙት፣ በቅርብ ጊዜያት በሱማሊያ በተፈጠሩ እንዳንድ ክስተቶች ዙሪያ ከአገሪቱ መሪዎች ጋር ለመወያየት እንደኾነ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ በሱማሊያና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት ከተፈጠረ ወዲህ፣ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ በኤርትራና ግብጽ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። ሶማሊላንድ ግን ከኢትዮጵያ ጋር ከተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ጋር...
በእታገኘሁ መኮነን 09/05/2016 የቀጠናው ሃገራት እና የቀጠናውን ጉዳይ በትኩረት የሚከታተሉ ሁሉ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ሐሙስ ጥር 9፤ 2016 በኡጋንዳ ኢንተቤ ከተማ ተካሂዷል፡፡ መሪዎቹ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ባወጡት መግለጫ ”የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛትን የሚመለከት ማንኛውም ስምምነት የሀገሪቱን መንግስት ይሁንታ ሊያገኝ ይገባል ” ብለዋል ፡፡መሪዎቹ ማንኛውም...
09/05/2016 የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ካምፓላ እና አዲስ አበባ ይጓዛሉ ብሏል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በመግለጫው ። አምባሳደር ሐመር በካምፓላ ፤ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ላይ በሚያተኩረው 42ኛው የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል። አምባሳደር ሐመር ከካምፓላ በኋላ...
09/05/2016 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት ትናንት ጥር 8/2016 ዓም በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ስላለው ሁኔታ ለመመካከር ስብሰባ አካሂዶ ነበር። የስብሰባው መርሐ ግብር ቀደም ተብሎ የተያዘ አልነበረም፡፡በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በሶማሊያ እና ኢትዮበሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት ስብሰባውን ማድረግ እንዳስፈለገ ምክርቤቱ ተናግሯል፡፡ የሶማሊያ ባለስልጣናት የሀገራቸውን ዳር...
ሱዳን፣ ኢጋድ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብቷል በማለት ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ዛሬ አስታውቃለች። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆነችው ጅቡቲ አቻቸው በጻፉት ደብዳቤ፣ ይህንኑ ውሳኔ አሳውቀዋል። ሱዳን ከኢጋድ ጋር ግንኙነቷን ያቋረጠችው፣ በመጭው ሐሙስ ኡጋንዳ ላይ የተጠራው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባዔ ወታደራዊውን መንግሥት ሳያማክር የሱዳኑን ጦርነት አጀንዳው ማድረጉንና የፈጥኖ ደራሹን ኃይል እንዲገኙ መጋበዛቸውን...
01/05/2016 ከኢትዮጵያ ጋር የወደብ ኪራይ ስምምነት ውል የገባችው ሶማሊላንድ ስምምነቱን በሚቃወሙ ሰዎች በሶማሊኛ ቋንቋ “ኢትዮጵያዊ ላይ በተገኘበት እርምጃ ይወሰድበት” የሚል በራሪ ጽሑፍ በሐርጌሳ ከተማ እየተበተነ መሆኑ ተነግሯል። በዚህም ምክንያት በሶማሊላንድ ለሚገኙ ከ 40 ሺ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በጣም አሳሳቢ ወቅት ሆኗል። በተለይም የኦሮሞ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ትኩረት በማድረግ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ለማድረስ፣...
ይህ ይፋ የተደረገው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC ከኢጋድ አባለ ሀገራት ለተወጣጡ ጋዜጠኞች በሰጠው ስልጠና ላይ ነው። ስልጠናው በዋናነት የበረሃ አንበጣና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ፀረ ሰብል ተባዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተለይ ባለፉት አራት አመታት በቀጠናው ክፉኛ የአንበጣ መንጋ ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የማዕከሉ ሪፓርት አመላክቷል። በጎረቤት...
