አካባቢ ጥበቃ

ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተተነበየ

ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተተነበየ

ይህ ይፋ የተደረገው የኢትዮጲያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የወቅቱን ትንበያ ይፋ ለማድረግ ባዘጋጀው የባለድርሻ አካለት መድረክ ነው። በመድረኩም ያለፈውን የበጋ ወቅት ትንበያ የገመገመ ሲሆን በጋው በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደተስተዋለባቸውና ይህም ሁኔታ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ለሚገኙ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ እንደነበረ ተገልጿል፡፡ በእለቱ የመጪው በልግ ትንበያ ይፋ የተደረገ ሲሆን በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል መደበኛና ከመደበኛ በታች፤ የቦረናና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ፤ የማዕከላዊና የደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛና ከመደበኛ በላይ፤ በሌላ በኩል የደቡብ ትግራይ፤ የምስራቅ አማራ፤ አፋር፤ መካከለኛው እና የምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መደበኛና…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደምታስተናግድ ኢጋድ ተነበየ።

ኢትዮጵያ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደምታስተናግድ ኢጋድ ተነበየ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC በቀጣይ አራት ወራት ማለትም ከሰኔ 2016 እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም  ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የሚኖረውን የዝናብ እና መጠነ ሙቀት ሁኔታ ትንበያ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ይፋ አድርጓል። ለኢትዮጵያ ክረምት በምንለው እና በሰሜኑ የምስራቅ አፍሪካ ክፍል በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ጁቡቲ፣ኤርትሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ዮጋንዳና ምዕራብ ኬንያን ጨምሮ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው ዝናብ በላይ እንደሚያገኙ የማዕከሉ ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ሁሴን ሰዒድ ተናግረዋል። ሁሴን አክለው በተለይ ለምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ፣ሰሜን፣ሰሜን ምስራቅ፣መካከለኛ የኢትዮጲያ ክፍል መጪው የክረምት በጣም ወሳኝ ወቅት ስለሆነ  ከፍተኛ ኤና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ያስተናግዳሉ። በመሆኑም…
ተጨማሪ ያንብቡ