ሙገሳ እና ወቀሳን በየፈርጁ ያስተናገደው ምርጫ 2018
እታገኘሁ መኮነን አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች መፈናቀሎች እና እገታዎች በሚስተዋሉበት ትግራይ ክልል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ራሱን ባገለለበት ፤ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙኃን ከዘገባ በታገዱበት ወቅት የተካሄደው የ2018ቱ ሃገራዊ ምርጫ ፤ ከአፍሪካ እና ከሃገር ውስጥ ታዛቢዎች ሙገሳን ከአንዳንድ የውጭ ታዛቢዎች እና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ወቀሳን አስተናግዶ አልፏል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫውን እንዳይዘግቡ ለታገዱ የውጭ ሚዲያዎች ፈቃድ እንዲሰጥ አስቀድሞ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በታዛቢነት እንዲገኙ የተፈቀደላቸው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምርጫው አለም አቀፍ መርሆዎችን ባከበረ መልኩ የተከናወነ ነው ሲሉ ምስክርነት ችረዋል፡፡አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልልሎች ውስጥ…
