ጋዜጠኛ አብነት ታምራት መታሰሩ ተሰምቷል።

14/06/2016

ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ በበርካታ ጋዜጣና መጽሔቶች በአዘጋጅነት ሲሰራ የቆየው ጋዜጠኛ አብነት ታምራት፣ የከተራ ዕለት በመንግስት የደህንነቶች ኃይሎች መያዙ ተሰምቷል።

አብነት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥሮ መያዙ የተሰማ ሲሆን ትላንትና ሰኞ ፍርድ ቤት አለመቅረቡን እና ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱ ታውቋል።