ምጣኔ ሃብት

ከተመን በላይ ነዳጅ የሚሸጡ ነጋዴዎችን እስከ አምስት አመት እስር እና እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ አዋጅ ጸደቀ፡፡አዋጁ ከምክር ቤት አባላት ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ከተመን በላይ ነዳጅ የሚሸጡ ነጋዴዎችን እስከ አምስት አመት እስር እና እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ አዋጅ ጸደቀ፡፡አዋጁ ከምክር ቤት አባላት ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 1 ቀን 2017 ባካሄደው ስብሰባ  መንግሥት ከተመነው የመሸጫ ዋጋ በላይ ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎች  ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እና እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር እንዲቀጡ የሚያደርግ አዋጅ  አጽድቋል፡፡ በአዋጁ መሠረት ከመሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ የሚፈጸም የመጀመሪያ ጥፋት ከሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል።ድርጊቱ በተደጋጋሚ ከተፈጸመ ከገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እንደሚኖር በአዋጁ ተደንግጓል። ድርጊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈጸም  ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ከተፈጸመ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት እስራት እና ከ350 ሺህ እስከ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – ሚቲዎሮሎጂ

በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – ሚቲዎሮሎጂ

በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚጥለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት እና የወንዞች ሙላት ሊያጋጥም ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ። በሚቀጥሉት 10 ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በዓባይ፣ ተከዜ፣ ባሮአኮቦ፣ ኦሞ፣ ጊቤ፣ አዋሽ፣ አፋር ደናክል፣ የላይኛውና የመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የላይኛው የገናሌ ዳዋና ዋቤ ሸበሌ ተፋሰሶች መካከለኛና በጣም ከፍተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተትና መሰንጠቅ፣ እንዲሁም የሰብል በጎርፍ የመጠረግ ሁኔታዎች እንዳይኖር መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎችም የሰብል በሽታ እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁሟል። በተጨማሪም በሚቀጥሉት 8 ቀናት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ…
ተጨማሪ ያንብቡ
 1 ነጥብ 7 ትሪሊየን ብር በቴሌብር ብቻ ማንቀሳቀስ ተችሏል -ኢትዮ ቴሌኮም

 1 ነጥብ 7 ትሪሊየን ብር በቴሌብር ብቻ ማንቀሳቀስ ተችሏል -ኢትዮ ቴሌኮም

14/06/2016 የቴሌ ብር አገልግሎት ከተጀመረ በኋላ በአጠቃላይ የግብይት መጠን 1 ነጥብ 7 ትሪልየን ብር በኢኮኖሚው ላይ ማንቀሳቀሱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም ይኼን የገለጸው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ስራ አፈጻጸሙን በዛሬው ዕለት ጥር 14 2016 በስካይ ላይት ሆቴል ባሳወቀበት መድረክ ነው። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴሌ ብር አገልግሎት ከ41 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራቱንም ተናግረዋል፡፡እንዲሁም በቴሌብር ሳንዱቅ፣ ቴሌ ብር እንደኪሴ፣ ቴሌብር መላ እና ሌሎችም የፉይናንስ አገልግሎት 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ደንበኞችን አፍርቶ፤ 8 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የብድር አገልግሎት እንዲሁም በቁጠባ አገልግሎት 8 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መቀመጡ ታውቋል። በተጨማሪም ከዲጂታል…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ የአጎዋ እድልን ዳግመኛ እንድታገኝ መንግስት ሰላም ለማምጣት መስራት አለበት ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ የአጎዋ እድልን ዳግመኛ እንድታገኝ መንግስት ሰላም ለማምጣት መስራት አለበት ተባለ፡፡

የሰሜን ኢትዮጵያዉን ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ ከተጣሉት ማዕቀቦች ዉስጥ አንዱ የአጎዋ ነጻ የንግድ እድልን ማጣት ነው፡፡ እገዳው አሁንም አልተነሳም፡፡የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጎሹ ነጋሽ  እንደተናገሩት ፤ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፉ በእቀባዉ መጎዳቱን ተናግረዉ ኢትዮጵያ የአጎዋ እድልን ዳግመኛ እንድታገኝ ሰላም በማምጣት በኩል የቤት ስራዋን መስራት አለባት ብለዋል።እግዱ ከተላለፈ በኋላ የታጣዉን የንግድ እድል ለማካካስ የተለያዩ ስራዎች በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መሰራታቸዉን ያነሱት አቶ ጎሹ ፤ የገበያ ትስስርን መፍጠር ዋነኛዉ መሆኑን ጠቁመዋል።ሀላፊው ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ባሉ የጨርቃጨርቅ አምራቾች የንግድ ትስስር ይፈጥራል የተብሎ የታመነበት አፍሪካ ሶርሲንግ እና የፋሽን ሳምንት ለ10ኛ ጊዜ በአዲስአበባ ስካይላይት ሆቴል ከጥቅምት 23- 26  እንደሚካሄድ…
ተጨማሪ ያንብቡ