እታገኘሁ መኮነን አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች መፈናቀሎች እና እገታዎች በሚስተዋሉበት ትግራይ ክልል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ራሱን ባገለለበት ፤ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙኃን ከዘገባ በታገዱበት ወቅት የተካሄደው የ2018ቱ ሃገራዊ ምርጫ ፤ ከአፍሪካ እና ከሃገር ውስጥ ታዛቢዎች ሙገሳን ከአንዳንድ የውጭ ታዛቢዎች እና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ወቀሳን አስተናግዶ አልፏል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት...
እታገኘሁ መኮነን የ2010ሩ ለውጥ እና የሚዲያው መነቃቃት 2010 ዓ.ም ፤የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የሃገር ግንባታ ሂደት ላይ ከታዩት ለውጦች መሃል አንዱ ለሚዲያው አንጻራዊ የሚባል ነጻ የመጫወቻ ሜዳ መፍቀድ ነበር ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም 2013 ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፀደቀ ፤የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013፡፡ ይሄ አዋጅ ከዛ ቀደም ብሎ...
ይህ ይፋ የተደረገው የኢትዮጲያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የወቅቱን ትንበያ ይፋ ለማድረግ ባዘጋጀው የባለድርሻ አካለት መድረክ ነው። በመድረኩም ያለፈውን የበጋ ወቅት ትንበያ የገመገመ ሲሆን በጋው በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደተስተዋለባቸውና ይህም ሁኔታ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ለሚገኙ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ እንደነበረ ተገልጿል፡፡ በእለቱ የመጪው...
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 1 ቀን 2017 ባካሄደው ስብሰባ መንግሥት ከተመነው የመሸጫ ዋጋ በላይ ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎች ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እና እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር እንዲቀጡ የሚያደርግ አዋጅ አጽድቋል፡፡ በአዋጁ መሠረት ከመሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ የሚፈጸም የመጀመሪያ ጥፋት ከሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር...
ረቂቅ አዋጁን በመቃወም 14 የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ እታገኘሁ መኮነን ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቅምት 19ቀን2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ...
በ-እታገኘሁ መኮነን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብች ኮሚሽን በኢትዮጵያ በአማራ ፣በኦሮሚያ ፣በማእከላዊ ኢትዮጵያ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ ክልል ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ሥጋቶች እና አሳሳቢ ሁኔታዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ የሩብ ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ግን በተለይ በግጭት ዐውድ...
አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ አስመራ እና ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ሲያደርግ የነበረውን በረራ ማቋረጡን ፋ ያደረገ ሲሆን አስቀድመው የበረራ ጉዞ ቲኬት የቆረጡ መንገደኞች ግን ያለምንም ዋጋ ጭማሪ በሌሎች አየር መንገዶች እንዲጓዙ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ ከነገ ነሀሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቆም አስታውቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ...
በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚጥለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት እና የወንዞች ሙላት ሊያጋጥም ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ። በሚቀጥሉት 10 ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በዓባይ፣ ተከዜ፣ ባሮአኮቦ፣ ኦሞ፣ ጊቤ፣ አዋሽ፣ አፋር ደናክል፣ የላይኛውና የመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የላይኛው የገናሌ ዳዋና ዋቤ ሸበሌ ተፋሰሶች መካከለኛና በጣም ከፍተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች...
እታገኘሁ መኮነን MELA ( Media Lawyers alliance )ተብሎ የተሰየመው ይህ የሚዲያ እና የህግ ባለሞያዎች ጥምረት በምስረታ ሂደት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ) ሰምተናል፡፡ ኅብረቱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በመሆን በጥምረቱ ዙሪያ ትናንት ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ)...
