ኢሰመኮ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ ለመቀጠል መወሰናቸውን አደነቀ
ዳዊት ታደሰ የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ኮሚሽን ህዳር 07 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤድ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጠውት የነበረውን የምግብ እርዳታ መልሰው ለመጀመር መወሰናቸው የሚወደስ ነው ብሏል፡፡ ኢሰመኮ በመግለጫው፣ በትግራይ ክልል ከባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ከሰኔ ወር ጀምሮ የተቋረጠውን የምግብ እህል እርዳታ ተከትሎ ስለተፈጠረው ሁኔታ ክትትል ሲያደርግ እንደነበር ዘርዝሯል፡፡ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ፍልሰተኞች በተለይ ደግሞ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ጋር ለመድረስ እንዲቻል አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ጨምሮ ሌሎች የማስተባበር ስራዎች በፍጥነት እንዲከወኑ ሲወተውት መቆየቱን ያስታወሰው ኮሚሽኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት…
