ሀገራዊ ምክክር

የአገራዊ ምክክር ሒደቱ በትግራይ ክልል እንዲጀመር ጥያቄ  ቀረበ

የአገራዊ ምክክር ሒደቱ በትግራይ ክልል እንዲጀመር ጥያቄ  ቀረበ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረበውን የሥራ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫ በማስመልከት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ውይይት  አድርጓል፡፡ በውይይቱም  የምክር ቤቱ አባላት በትግራይ ክልል የሃገራዊ ምክክር ሒደት እንዲጀመር ጠይቀዋል፡፡  ለምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር)፣ ከትግራይ ክልል ውጪ የአማራ ክልልን ጨምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተባባሪዎች ሥልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የተሳታፊ ልየታና መረጣ ባሉት ነባራዊ ሁኔታዎች ምክንያት በአማራና በትግራይ ክልሎች አለመጀመሩን ተናግረዋል፡፡  በአማራ ክልል ባለው ግት ምክንያት 800 ያህል ለሚሆኑ ተባባሪዎች ሥልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ200 ያህሉ ብቻ መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡ በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ምንም ዓይነት ሥራዎችን…
ተጨማሪ ያንብቡ
በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ

በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በመወከል በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 27፣ 2017 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የርክክብ ስነ ስርዓት፤ ፤ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ “ሊመከርባቸው ይገባሉ” ብለው የመረጧቸውን ጉዳዮች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ምክር ቤት አስረከቡ። ተወካዮቹ አጀንዳዎቻቸውን በስምንት ርዕሰ ጉዳዮች በመከፋፈል  ያቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና አወቃቀር፣ ቋንቋ፣  ታሪክ እና ትርክት፣ የሃገረ መንግስት ግንባታ እና የሃገር አንድነትን፣ የአንድነት እና ብዝሃነትን የሰንደቅ አላማ እና የህገ መንግስት ጉዳዮችን የተመለከቱ ይገኙበታል ተብሏል። አሁን በስራ ላይ ካለውን የኢፌዲሪ ህገ መንግስት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሴቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ ይችላሉ?

ሴቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ ይችላሉ?

በኢትዮጵያ ሴቶች ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ከ50 በመቶ በላይ እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ቢያመለክቱም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ግን ከቁጥራቸው አንፃር እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ ነው ጥናታዊ መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ሲያስተባብር በቆየው የምክክር ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ በሚገባቸው ልክ ለማድረግ ተጨባጭ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ የእስካሁኑ የኮሚሽኑ ጥረት እንዳለ ሆኖ ኮሚሽኑ በቅርቡ በሚያስተባብረው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሴቶችን ተሳትፎ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡ ታዲያ ሴቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ ይችላሉ? 1. የማህበረሰብ ክፍሎችን በመወከል በኮሚሽኑ ከተለዩት ባለድርሻ አካላት መካከል የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሽ ባለድርሻ አካል ናቸው፡፡ ከእነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች አንዱ ሴቶች…
ተጨማሪ ያንብቡ
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ምክክር ላይ በአጀንዳነት የሚቀርቡ ጉዳዮችን እንዲያዘጋጁ ተጠየቁ::

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ምክክር ላይ በአጀንዳነት የሚቀርቡ ጉዳዮችን እንዲያዘጋጁ ተጠየቁ::

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ “አጀንዳ ሊሆኑ ይገባሉ” የሚሏቸውን እና በሃገራዊ ምክክር ላይ ሊቀርቡ የሚገቡ  ጉዳዮች እንዲያዘጋጁ  ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረበ።  ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሚያቀርቧቸው አጀንዳዎች ላይ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የሚያካሄዱበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች አስታውቋል።  ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በላከው ደብዳቤ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በላከው ደብዳቤ፤ ፓርቲዎቹ በሚያቀርቧቸው አጀንዳዎች ላይ “ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመገናኘት ውይይት የሚያካሄዱበትን ሁኔታ በቀጣይ የሚያሳውቅ መሆኑን” አመልክቷል።  የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት “አጀንዳዎችን የመሰብሰብ ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ” በማንሳት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ “ለሀገራዊ ምክክር ሊቀርብ ይገባል” የሚሏቸውን “የአጀንዳ ነጥቦች” የማዘጋጀት ስራ እንዲያከናውኑ…
ተጨማሪ ያንብቡ
<<ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የመለየት ስራ በቅርቡ ይጀመራል፡፡>>

<<ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የመለየት ስራ በቅርቡ ይጀመራል፡፡>>

12/04/2016 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በፅህፈት ቤቱ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ በ327 ወረዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ መነሳት አለባቸው ያሏቸውን አጀንዳዎች የሚለዩ ተሳታፊዎች መለየታቸውን አስታውቋል። ከትግራይና ከአማራ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ለምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የሚለዩና በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ ተወካዮች መምረጣቸውን የጠቀሱት ኃላፊው መዲናዋን ጨምሮ የተሳታፊዎች ልየታ በተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች ለምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ለመለየት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። በተለያዩ የአገሪቱ 700 ወረዳዎች ላይ የተሳታፊዎች ልየታ እየተከናወነ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ 327 ወረዳዎች የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮችን መመርጣቸውን ጠቁመዋል። በአማራ እና በትግራይ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የምክክር ኮሚሽኑ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እና በስድስት ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

የምክክር ኮሚሽኑ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እና በስድስት ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ባለፉት 4 ወራት አዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በ6 ክልሎች የሃገራዊ ምክክር የተሳታፊዎች ልየታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የ4 ወራት አፈጻጸም ረፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን  የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የ4 ወራት አፈጻጸም ሪፖርትንም አዳምጧል፡፡ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ በቅድመ ዝግጅት ስራው ከእድሮች፣ ከሃማኖት ተቋማት፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከመምህራን ማህበር ጋር በአጋርነት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በመላ ሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው የተሳታፊዎች ልየታና የአጀንዳ ማሰባሰብ ተግባር ሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በ6 ክልሎች  ላይ በተለይ የልየታ ስራው…
ተጨማሪ ያንብቡ