ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰየሙ

ሰኞ ጥቅምት 26 / 2016

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰይመዋል።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል።

በዚሁ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሰየሙ የዕጩ ሰብሳቢ መልማይ ኮሚቴ አባላት፡-

1.  ቀሲስ ታጋይ ታደለ…………….. ሰብሳቢ

2.  ተከተል ዮሐንስ (ፕ/ር) ………….አባል

3.  ባዩህ በዛብህ…………. አባል

4.  ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) …………. አባል

5.  ካሳሁን ፎሎ…………. አባል

6.  ርግበ ገብረሃዋርያ…………. አባል

7.  እንግዳዬ እሸቴ…………. አባል

8.  መላኩ እዘዘው (ኢ/ር) …………. አባል ናቸው።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴው ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፤ በቅርቡም ጥቆማ መቀበል ይጀምራል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡