የምግብ ድጋፍ አቅርቦት እገዳ ባለመነሳቱ በምግብ እጥረትና ሰብአዊ ቀውስ ላይ ያሳደረው ጫና እንደቀጠለ ነው።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ለተፈናቃዮች እየቀረበ ያለውን የምግብ ድጋፍ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት (USAID) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የምግብ ድጋፍ ለስደተኞች እንዲጀመር ማድረጋቸው በጎ እርምጃ ሆኖ፤ በአንጻሩ ለተፈናቃዮች እና ለሌሎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚሰጠው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት እገዳ አለመነሳቱ በምግብ እጥረትና ሰብአዊ ቀውስ ላይ ያሳደረው ጫና እንደቀጠለ ነው ብሏል::የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የተሟላ እና በቂ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቢኖርም፣ ባለፉት ወራት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች ትኩረት በመስጠት በሁለት ዙር በአፋር ክልል 96%፣ በጋምቤላ 96%፣ በትግራይ 87%፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 73%፣…
