ስደተኞችን በማስጠለል ከአፍሪካ ቀዳሚ የነበረችው ኢትዮጵያ በ3ኛነት ተቀመጠች::
ለበርካታ ዓመታት በአፍሪካ በአንደኝነት ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ አስጠልላ የቆየችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሶስተኛዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ተጠልሎባት የሚገኝ ሀገር ናት ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ሱዳንን እና ኡጋንዳን በመከተል በሶስተኝነት ስደተኞችን ያስጠለለችው ኢትዮጵያ 954ሺ ከተለያዩ ሀገራት ድንበሯን አቋርጠው የገቡ ስደተኞች እንደሚገኙባት ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃ ጠቁሟል። የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ዩኤንኤችሲአር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሱዳናውያን ናቸው። ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞች በሁለተኝነት እና በሶስተኝነት ተቀምጠዋል። ኢትዮጵያ በሁሉም ድንበሮቿ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች እንዲገቡ በሮቿን ክፍት ማድረጓን የጠቆመው የመንግስታቱ…
