ሀገርኛ

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሌላ ዙር ውይይት ይጀምራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለፁ::

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሌላ ዙር ውይይት ይጀምራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለፁ::

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድርን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል። ዶ/ር ወርቅነህ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ውይይት እና ድርድር ያለውን ወሳኝ ሚና እንደሚገነዘቡ ገልጸዋል። ኢጋድ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ውይይት ላይ በቅርበት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ በማንኛውም የድርድር ሂደት ውስጥ የማይቀር የፈተና ጊዜያት እንዳሉ እንደሚገነዘቡ መሰል የሽምግልና ሂደቶችን ልምድ በመንተራስ ገልጸዋል። ዶ/ር ወርቅነህ ሁለቱም ተደራዳሪ ቡድኖች አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰላማዊ ውይይት ማድረጋቸውን አመስግነው ለኢጋድ የቴክኒክ ቡድን እና ታዛቢዎች በተለይ ደግሞ የአሜሪካ እና የኖርዌይ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት 2ኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት  አበቃ

የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት 2ኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት አበቃ

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያዋ ዳሬሰላም ከተማ ለቀናት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለውጤት መበተኑን መንግሥት አስታወቀ። ይህንን ያሳወቁት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና መንግሥትን ወክልው በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ናቸው። አምባሳደር ሬድዋን በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ላይ ማክሰኞ ኅዳር 11/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ባሰራጩት መልዕክት እንዳሉት ሲካሄድ የሰነበተው ድርድር ካለስምምነት በመጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዘኑን አመልክተዋል። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ በታንዛኒያ የመዝናኛ ደሴት ዛንዚባር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግሥት እና በአማጺው መካከል በተመሳሳይ ለቀናት የቆየ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል። ሁለተኛው ዙር ድርድር ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በታንዛኒያ ዋና…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ  አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ የተወሰኑ  ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ  ለማሰራት ወሰኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ  አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ የተወሰኑ  ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ  ለማሰራት ወሰኗል፡፡

ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔውን ለመወሰን የሚያስችል በቂ ጥናት እና ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል፡፡ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉት ሥራዎች ግን ተለይተው አልተገለፁም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን በማዕከል ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ወደ ወረዳና ሌሎች ተቋማት ምደባ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
በደብረማርቆስ ከጸጥታ እክል ጋር በተያያዘ ወላድ እናቶች ለችግር ተዳርገዋል

በደብረማርቆስ ከጸጥታ እክል ጋር በተያያዘ ወላድ እናቶች ለችግር ተዳርገዋል

ለአለምበአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች እየተከሰቱ ባሉ ግጭቶች በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ጉዳት እየደረሰ እንደሆነ ነዋሪዎች ለአዲስ ጊዜ ገለጹ። ግጭቱ ተደጋግሞ እያጋጠመ ባለበት በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ  ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የሚናገሩት ወ/ሮ  ማዕረግ  ሞላ በሚኖሩበት አካባቢ በተከሰተው ጦርነት ይበልጥ ተጎጂ እየሆኑ ያሉት እናቶችና ህፃናት እንደሆኑ ተናግረዋል።በደብረ ማርቆስ ዙሪያ ረቡዕ ገበያ ነዋሪ የሆኑት የጤና ባለሞያ አቶ አለምእሸት ስንሻው በበኩላቸው የመድሀኒት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት እየታየበት መሆኑን ገልፀው በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የጤና ጣቢያዎችን በቋሚነት ለመክፈት መቸገራቸውን ገልፀዋል።በዚህም ሳቢያ እናቶች በቤታቸው ለመውለድ እንደተገደዱ የሚገልፁት የጤና ባለሞያው፤ በተለይ የደረሱ ሴቶች በእርግዝና ወራት ሊያገኙት የሚገባ የጤና ክትትል በበቂ ሁኔታ ባለመውሰዳቸው ከፍተኛ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ዩ.ኤስ.ኤድ ያቋረጠውን ርዳታ ሊጀምር ነው

ዩ.ኤስ.ኤድ ያቋረጠውን ርዳታ ሊጀምር ነው

ዩኤስኤድ ከወራት በፊት አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ከቀጣይ ወር ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ እንደሚጀምር ማስታወቁ ተዘግቧል።በኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጎጂዎች ተብሎ የሚቀርብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑ በመረጋገጡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡ ይታወሳል። ዩ.ኤስ.ኤድ በመላ ሀገሪቱ ለአንድ አመት ያክል የእርዳታ ስርጭቱን በማካሄድ ለመሞከር ማቀዱን አስታውቋል ያለው የሮይተርስ ዘገባ በዚህ የሙከራ ጊዜ የምግብ እርዳታውን አቅርቦት ለሚገባቸው ተረጂዎች መዳረሱን ክትትል እንደሚያደርግ እና ምርምራ እንደሚያከናውን መግለጹን አመላክቷል። የረድኤት ድርጅቱ የምግብ አቅርቦቱን የሚጀምረው ለበርካታ ወራት ከመንግስት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች ከተከናወኑ በኋላ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው የኢትዮጵያ መንግስት እና አጋር አካላት ከእርዳታ እደላ ጋር በተያያዘ እጅግ አስፈላጊ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፓርላማ ውሎ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፓርላማ ውሎ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዶ ነበር። የምክር ቤት አባላትም ማብራሪያ ቢሰጥባቸው ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይም ምላሽ ያሉትን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በብዙዎች ዘንድ አወዛጋቢ በተባለ በዚህ ገለፃቸው ላይ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን አዲስ ጊዜ ሚዲያም አንኳር ነጥቦቹን እንዲህ አሰናድታዋለች፡፡ መንግሥትን በኃይል ስለመገዳደር ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ትጥቅን የቀላቀሉ ትግሎችን የሚመለከተው አንደኛው ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ግጭት ወደሰላም ለማምጣት ምን እየተደረገ እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠ/ሚንስትሩ ምላሻቸውን ሲጀምሩ "ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ መንግሥትን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ስደተኞችን በማስጠለል ከአፍሪካ ቀዳሚ የነበረችው ኢትዮጵያ በ3ኛነት                       ተቀመጠች::

ስደተኞችን በማስጠለል ከአፍሪካ ቀዳሚ የነበረችው ኢትዮጵያ በ3ኛነት ተቀመጠች::

ለበርካታ ዓመታት በአፍሪካ በአንደኝነት ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ አስጠልላ የቆየችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሶስተኛዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ተጠልሎባት የሚገኝ ሀገር ናት ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ሱዳንን እና ኡጋንዳን በመከተል በሶስተኝነት ስደተኞችን ያስጠለለችው ኢትዮጵያ 954ሺ ከተለያዩ ሀገራት ድንበሯን አቋርጠው የገቡ ስደተኞች እንደሚገኙባት ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃ ጠቁሟል። የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ዩኤንኤችሲአር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሱዳናውያን ናቸው። ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞች በሁለተኝነት እና በሶስተኝነት ተቀምጠዋል። ኢትዮጵያ በሁሉም ድንበሮቿ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች እንዲገቡ በሮቿን ክፍት ማድረጓን የጠቆመው የመንግስታቱ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የምክክር ኮሚሽኑ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እና በስድስት ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

የምክክር ኮሚሽኑ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እና በስድስት ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ባለፉት 4 ወራት አዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በ6 ክልሎች የሃገራዊ ምክክር የተሳታፊዎች ልየታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የ4 ወራት አፈጻጸም ረፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን  የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የ4 ወራት አፈጻጸም ሪፖርትንም አዳምጧል፡፡ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ በቅድመ ዝግጅት ስራው ከእድሮች፣ ከሃማኖት ተቋማት፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከመምህራን ማህበር ጋር በአጋርነት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በመላ ሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው የተሳታፊዎች ልየታና የአጀንዳ ማሰባሰብ ተግባር ሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በ6 ክልሎች  ላይ በተለይ የልየታ ስራው…
ተጨማሪ ያንብቡ
አምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ የሥነ-ሕዝብ እና ጤና ጥናት በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ውስጥ ይካሄዳል ተባለ ::

አምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ የሥነ-ሕዝብ እና ጤና ጥናት በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ውስጥ ይካሄዳል ተባለ ::

በአሸናፊ አሰበ የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት በየአምስት አመቱ የሚካሄድ ሲሆን አራተኛው ጥናት እ.አ.አ በ2016 ከወጣ በኋላ ሳይወጣ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በበኩሉ አምስተኛው ዙር የሥነ ሕዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት በኮቪድ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ምክንያቶች መሰራት ከነበረበት ጊዜ በሁለት ዓመት መጓተቱን ገልጾ በተያዘው በጀት ዓመት መጋቢት ወር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀስ እንደሆነ የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የመረጃ ስርጭት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ለአዲስ ጊዜ ገልጸዋል። ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም በሚቆየው የስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም ትግበራ ወቅት በሚካሄዱት ቆጠራዎችና ጥናቶችን በሚመለከት ሲከናወኑ በነበሩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ ቆጣሪዎችን እየቀየረ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ ቆጣሪዎችን እየቀየረ ነው።

በአሸናፊ አሰበ ደምበኞች በቀላሉ አፕልኬሽኑን ሞባይላቸዉ ላይ በመጫን ያላቸዉን ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በቀላሉ ለማወቅ፣ ከቆጣሪ ንባብ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን  ለማስቀረት፣ የሃይል ስርቆትን ለመከላከል፣ የንባብ ስህተት ችግርን ለመቅረፍ እና ለመከላከል እንደሚያስችል የተነገረለት የዘመናዊ ቆጣሪ ቅየራ ስራ ሁለተኛ ዙር እንደተጀመረ  የፕሮጀክቱ ሃላፊ አቶ ጩመላ ሣሙኤል ለአዲስ ጊዜ ተናግረዋል። የመጀመሪያው ትግበራ ሚያዚያ 2015 ዓም መጀመሩን እና በሙከራው ሂደት 5000 የስማርት ቆጣሪዎችን ማዳረስ መቻሉን የተናገሩት አቶ ሣሙኤል የፕሮጀክቱ ትግበራ በዋናነት የተጀመረው ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ በሆኑ ወይም የሃይል ፍጆታቸው ከ 25 ኪሎ ዋት(KW) በላይ በሚጠቀሙ የማሕበረሰብ ክፍሎች ላይ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ትግበራ 45 ሺህ ነባር ቆጣሪዎችን በ6 ወር ጊዜ ውስጥ…
ተጨማሪ ያንብቡ