የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ  አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ የተወሰኑ  ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ  ለማሰራት ወሰኗል፡፡

ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔውን ለመወሰን የሚያስችል በቂ ጥናት እና ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል፡፡ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉት ሥራዎች ግን ተለይተው አልተገለፁም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን በማዕከል ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ወደ ወረዳና ሌሎች ተቋማት ምደባ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡