አዲስ ጊዜ

230 Posts
አምስት ‘አደገኛ’ ታራሚዎች ከቱኒዚያ እስርቤት አመለጡ 

አምስት ‘አደገኛ’ ታራሚዎች ከቱኒዚያ እስርቤት አመለጡ 

በቱኒዚያ ከሚገኝ እስር ቤትየተኒዚያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ፎቶግራፋቸውን በማጋራት ዜጎች ራሳቸውን ከእነዚህ ግለሰቦች እንዲጠብቅና ማንኛውንም መረጃ እንዲሰጥ ጠይቋል።እስረኞቹ ማክሰኞ ማለዳ ከሞርናጊያ ማረሚያ ቤት አምልጠዋል ሲል ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገፁ ላይ አጋርቷል። በ2013 ሁለት ፖለቲከኞችን በመግደል ለእስር የተዳረገው አህመድ ማልኪ ካመለጡት መካከል አንዱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።እ.ኤ.አ. በ2013 የተፈፀመው ግድያ በቱኒዚያ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በማስከተል በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበረው መንግስት ስልጣን እንዲለቅ አስገድዶታል።ካመለጡት እስረኞች መካከል ሬይድ ቱዋቲንም ያለበት ሲሆን የጸጥታ ምንጮች እንደሚሉት ባለፉት አስርት አመታት ቱኒዚያን ያንቀጠቀጠው እጅግ አስከፊ ጥቃት የመራ ሰው ስለመሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል።ቱኒዚያ በ2011 የረዥም ጊዜ ገዢውን ዚን አል-አቢዲን ቤን አሊን ከስልጣን በማስወገድ የአረብ አብዮት መነሻ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ማድረጉን የጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ማድረጉን የጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

ጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ "በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እና በአካባቢው አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ መሻሻል እየመጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ መልኩ ማከናወን እንዲችል የሰው፣ የባጃጅና ሆቴሎች  የስራ ሰዓት ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።" ሲል ገልፆል። በዚህም መሠረት ከዛሬ ጥቅምት 21/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ መንቀሳቀስ የሚቻለው ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አሳውቋል።  ከዚህ ውጪ የተለየ እንቅስቃሴ በሚያደርግ ማንኛውም አካል  ላይ ኮማንድ ፖስቱ  በሚወስደው ህጋዊ እርምጃ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን አክሎ አሳውቋል፡፡ መረጃውን ያገኘነው ከወልቂጤ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሥራዉን በይፋ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሥራዉን በይፋ ጀመረ።

ኮሚሽኑ በክልሉ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትን   አስመልክቶ በሆሳዕና ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የኮሚሽኑ  ኮሚሽነር  ዶክተር ዮናስ አዳዬ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ለኮሚሽኑ ከወዲሁ እያሳየ ላለዉ ትብብር አመስግነዉ ይህም ለኮሚሽኑ አዎንታዊ ዉጤት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በበኩላቸው ኮሚሸኑ የተቋቋመበትን ህጋዊ መሠረት ጠቅሰዉ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከነገ ጀምሮ  በሆሳዕና ከተማ ለተባባሪ አካላት ሥልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። ለሦሥት ተከታታይ ቀናት በሚቆየዉ ሥልጠና ከተለያዩ ማኅበራዊ መሠረት የተዉጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሥልጠናዉ የምክክር ጽንሰ-ሀሳብ፣ አላማ፣ ሂደት፣ አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች የተመለከቱ   ርዕሰ-ጉዳዮች ይቀርባሉ ተብሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር  1265/2014 ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል።  መረጃዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሚንኬሽን…
ተጨማሪ ያንብቡ
“ሜታ በትግራይ ተወላጆች ላይ ለሚደርሰው ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት አስተዋጽኦ አድርጓል” አምነስቲ ኢንተርናሽናል

“ሜታ በትግራይ ተወላጆች ላይ ለሚደርሰው ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት አስተዋጽኦ አድርጓል” አምነስቲ ኢንተርናሽናል

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የትግራይ ተወላጆች ላይ በማነጣጠር ለተሰነዘሩ ማንነት ተኮር ጥቃቶች የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ተባባሪ ሆኗል ሲል የአለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወቀሰ፡፡ አምነስቲ ትናንት ጥቅምት 20/2016 ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ "ሜታ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል" ያለ ሲሆን፤ ኩባንያው ጥላቻ እና ጥቃትን የሚያበረታቱ ይዘቶችን በበቂ ሁኔታ መቆጣጠርና መግታት አለመቻሉን ገልጿል፡፡ በዚህም “ፌስቡክ የሚከተለው ደካማ የንግድ ሞዴል እና መረጃዎችን የመቆጣጠር እንቅስቃሴ፤ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ እና የቅስቀሳ ዘመቻዎችን እንዳይቆጣጠር አድርጎታል” ያለ ሲሆን፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ወቅት በትግራይ ማህበረሰብ ላይ ለደረሰው ግፍ ኩባንያው የራሱን…
ተጨማሪ ያንብቡ
1.5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል የተባለ ስምምነት ተፈረመ::

1.5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል የተባለ ስምምነት ተፈረመ::

ሰኞ ጥቅምት 19/2016 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችን እና ወጣቶችን አቅም በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል ያለውን የመግባቢያ ስምምነት ሄይፈር ኢንተርናሽናል ከተሰኘ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር ዛሬ ጥቅምት 19 2016 ዓ.ም በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ተፈራርሟል። ስምምነቱን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ከ ሄይፈር ኢንተርናሽናል ምክትል ፕሬዝዳንት ኤዲስዋ ኢፌዲ  ጋር የተፈራረሙ ሲሆን ከ 1 ሚሊየን እስከ 1.5 ሚሊየን ለሚጠጉ ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ታምኖበታል። ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በአመት እስከ 3 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ሙፈርያት ባለፈው በጀት አመት 3.5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኬንያ የሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች ያለቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው።

ኬንያ የሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች ያለቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው።

ኬንያ የቪዛ ገደቦችን በማንሳት ሁሉም አፍሪካውያን ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ ግዛቷ መግባት እንዲችሉ በሯን ለመክፈት መዘጋጀቷን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ገለጹ። “አሁን የቪዛ ክልከላዎች አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠሩብን መሆኑን የተገነዘብንበት ወቅት ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ይህ ለአፍሪካውያን የቪዛ ጥያቄን ለማስቀረት የሚያስችለው የኬንያ ሃሳብ ባለንበት የአውሮፓውያን ዓመት ማብቂያ፣ ማለትም በመጪዎቹ ሁለት ወራት ተግባራዊ እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ገልጸዋል። በአህጉሪቱ አገራት መካከል ከቪዛ ነጻ ጉዞ እንዲኖር ማድረግ ከአፍሪካ ኅብረት ያለፉት ዓመታት ግቦች አንዱ ነበር።በ2022 (እአአ) በወጣ አንድ ሪፖርት መሠረት ሲሸልስ፣ ጋምቢያ እና ቤኒን ብቻ ናቸው እስካሁን ለአህጉሪቱ ዜጎች ከቪዛ ነጻ ጉዞን የፈቀዱት። ፕሬዝዳንት ሩቶ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ቅዱስ ሲኖዶሱ በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶሱ በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ።

ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ስለ አገር ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከሕዳር 15/2016 እስከ ታህሣሥ 27/2016 ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት መላው ሕዝበ ክርስቲያን በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን አቅርቧል፡፡   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ከጥቅምት 11/2016 ጀምሮ ሲያካሂደው የቆየውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ መጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። በስብሰባውም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቷ እንዲሁም ስለተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በስተቀር የወለድ ክፍያ ያለበትን የብድር ውል ማዋዋል እንደማይችል ተገልጿል።

ከባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በስተቀር የወለድ ክፍያ ያለበትን የብድር ውል ማዋዋል እንደማይችል ተገልጿል።

ጥቅምት 19/2016 በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ግለሰቦች ወይም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ያሉ የንግድ ድርጅቶች፣ በመካከላቸው የሚያደርጉትን የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማዋዋል እንደማይቻል ብሔራዊ ባንክ አስጠንቅቋል። የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማበደር የሚችለውና ገንዘብ መሰብሰብ የሚችለው ባንክና ማይክሮ ፋይናንስ ብቻ በመሆኑ፣ ግለሰቦች ወለድ በማስከፈል ማበደር አይችሉም " ሲሉ የብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ፈቃዱ ደግፌ አስረድተዋል፡፡ የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እንደሚገልጸው፣ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ውጪ፣ ቁጠባ እንዲሰበስቡና ብድር እንዲሰጡ በልዩ ሕግ የተፈቀደላቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ገንዘብ የሚያበድሩ ግለሰቦች በወንጀል የሚያስቀጣቸው ተግባር በመሆኑ፣ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ማንኛውም የወለድ ክፍያ ያለበት የብድር…
ተጨማሪ ያንብቡ
በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት  ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመመለሳቸው እንዳሳሰባቸው  በክልሉ የሚገኙ የተማሪ ወላጆች ገለፁ።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት  ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመመለሳቸው እንዳሳሰባቸው  በክልሉ የሚገኙ የተማሪ ወላጆች ገለፁ።

ሰኞ ጥቅምት 19/2006 ካለፈዉ ሀምሌ ወር ጀምሮ በተፈጠረው የአማራ ክልል ግጭት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች አሁንም ከዕውቀት ገበታ ውጭ እንደሆኑ የተማሪ ወላጆች  ለአዲስ ጊዜ ተናግረዋል ፡፡ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደሚገኙ ያነሱነት ወላጆች  በክልሉ አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች የመማር ማስተማሩ ሥራ እንደወትሮውም ባይኾን መቀጠሉን አንስተዋል። ባለፉት ዓመታት በነበረው ጦርነት ከፍተኛ ሥነ ልቦናዊ ጫና ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እንዳሉ አንስተው አሁንም በቀጠለው የሰላም እጦት ምክንያት ልጆቻቸው በከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ላይ እንደሚገኙ ወላጆች ተናግረዋል፡፡ አስተያየታቸውን ለአዲስ ጊዜ የሰጡ በክልሉ የሚገኙ መምህራን በበኩላቸው የወደሙና ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እና ተማሪዎችን ወደ ዕውቀት ገበታቸው ለመመለስ መንግሥት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የድምጽ ብክለት ቁጥጥርን በተመለከተ ያዘጋጀው አዲስ ረቂቅ ደንብ እስካሁን አልጸደቀም ተባለ ።

የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የድምጽ ብክለት ቁጥጥርን በተመለከተ ያዘጋጀው አዲስ ረቂቅ ደንብ እስካሁን አልጸደቀም ተባለ ።

ሰኞ ጥቅምት 19/2016 በ1995 ዓ.ም የወጣውን የብክለት ቁጥጥር አዋጅ 300/1995 አንቀጽ 20 መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው የተባለው እና በ 2011 ዓ.ም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ የተላከው ደንብ እስካሁን አለመፅደቁን በኮሚሽኑ የአካባቢ ብክለት ሁኔታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ወይዘሮ ሙሉብርሃን ታሪኩ ለአዲስ ጊዜ ተናገሩ። በ አዲስ አበባ የሚታየው ከፍተኛ የድምጽ ብክለት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን በድምጽ ማጉያ የታጀቡ  የንግድ ማስታወቂያዎች፣ ሃይማኖታዊ   መልዕክቶች፣ እና ከንግድ ቤቶች የሚለቀቁ ቅጥ ያጡ ሙዚቃዎችን መታዘብ ከጀመርን ዋል አደር ብሏል። ይህንን የድምጽ ብክለት ለመከላከል ምን  ተሰራ ስንል ከአዲስ ጊዜ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ብክለቱን ለመከላከል እንዲሁም አጥፊዎችን ለማስቀጣት  ያግዛል ያልነውን ደንብ በእኛ በኩል  አዘጋጅተን…
ተጨማሪ ያንብቡ