አምስት ‘አደገኛ’ ታራሚዎች ከቱኒዚያ እስርቤት አመለጡ 


በቱኒዚያ ከሚገኝ እስር ቤትየተኒዚያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ፎቶግራፋቸውን በማጋራት ዜጎች ራሳቸውን ከእነዚህ ግለሰቦች እንዲጠብቅና ማንኛውንም መረጃ እንዲሰጥ ጠይቋል።
እስረኞቹ ማክሰኞ ማለዳ ከሞርናጊያ ማረሚያ ቤት አምልጠዋል ሲል ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገፁ ላይ አጋርቷል። በ2013 ሁለት ፖለቲከኞችን በመግደል ለእስር የተዳረገው አህመድ ማልኪ ካመለጡት መካከል አንዱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

እ.ኤ.አ. በ2013 የተፈፀመው ግድያ በቱኒዚያ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በማስከተል በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበረው መንግስት ስልጣን እንዲለቅ አስገድዶታል።ካመለጡት እስረኞች መካከል ሬይድ ቱዋቲንም ያለበት ሲሆን የጸጥታ ምንጮች እንደሚሉት ባለፉት አስርት አመታት ቱኒዚያን ያንቀጠቀጠው እጅግ አስከፊ ጥቃት የመራ ሰው ስለመሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል።

ቱኒዚያ በ2011 የረዥም ጊዜ ገዢውን ዚን አል-አቢዲን ቤን አሊን ከስልጣን በማስወገድ የአረብ አብዮት መነሻ ሆናለች። ፕሬዚደንት ካይ ሳኢድ አጠቃላይ ስልጣንን ለመያዝ ሲሞክሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የፖለቲካ ውዥንብር ገጥሟታል። ከቱኒዚያ አስከፊ ጥቃቶች አንዱ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2015 አንድ ታጣቂ ከሱሴ በስተሰሜን በሚገኝ ታዋቂ ሪዞርት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቱሪስቶች ላይ ተኩስ ከፍቶ ሰላሳ ስምንት ሰዎች የተገደሉበት ክስተት ይታወሳል።