የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሥራዉን በይፋ ጀመረ።

ኮሚሽኑ በክልሉ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትን   አስመልክቶ በሆሳዕና ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ  ኮሚሽነር  ዶክተር ዮናስ አዳዬ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ለኮሚሽኑ ከወዲሁ እያሳየ ላለዉ ትብብር አመስግነዉ ይህም ለኮሚሽኑ አዎንታዊ ዉጤት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በበኩላቸው ኮሚሸኑ የተቋቋመበትን ህጋዊ መሠረት ጠቅሰዉ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከነገ ጀምሮ  በሆሳዕና ከተማ ለተባባሪ አካላት ሥልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ለሦሥት ተከታታይ ቀናት በሚቆየዉ ሥልጠና ከተለያዩ ማኅበራዊ መሠረት የተዉጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሥልጠናዉ የምክክር ጽንሰ-ሀሳብ፣ አላማ፣ ሂደት፣ አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች የተመለከቱ   ርዕሰ-ጉዳዮች ይቀርባሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር  1265/2014 ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል። 

መረጃዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሚንኬሽን ቢሮ ነዉ።