ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016
ስለ አገር ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከሕዳር 15/2016 እስከ ታህሣሥ 27/2016 ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት መላው ሕዝበ ክርስቲያን በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ከጥቅምት 11/2016 ጀምሮ ሲያካሂደው የቆየውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ መጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
በስብሰባውም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቷ እንዲሁም ስለተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡
