በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ማድረጉን የጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

ጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ “በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እና በአካባቢው አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ መሻሻል እየመጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ መልኩ ማከናወን እንዲችል የሰው፣ የባጃጅና ሆቴሎች  የስራ ሰዓት ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።” ሲል ገልፆል።

በዚህም መሠረት ከዛሬ ጥቅምት 21/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ መንቀሳቀስ የሚቻለው ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አሳውቋል።  ከዚህ ውጪ የተለየ እንቅስቃሴ በሚያደርግ ማንኛውም አካል  ላይ ኮማንድ ፖስቱ  በሚወስደው ህጋዊ እርምጃ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን አክሎ አሳውቋል፡፡

መረጃውን ያገኘነው ከወልቂጤ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።