ጥቅምት 19/2016
በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ግለሰቦች ወይም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ያሉ የንግድ ድርጅቶች፣ በመካከላቸው የሚያደርጉትን የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማዋዋል እንደማይቻል ብሔራዊ ባንክ አስጠንቅቋል።
የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማበደር የሚችለውና ገንዘብ መሰብሰብ የሚችለው ባንክና ማይክሮ ፋይናንስ ብቻ በመሆኑ፣ ግለሰቦች ወለድ በማስከፈል ማበደር አይችሉም ” ሲሉ የብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ፈቃዱ ደግፌ አስረድተዋል፡፡
የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እንደሚገልጸው፣ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ውጪ፣ ቁጠባ እንዲሰበስቡና ብድር እንዲሰጡ በልዩ ሕግ የተፈቀደላቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡
በተመሳሳይ መንገድ ገንዘብ የሚያበድሩ ግለሰቦች በወንጀል የሚያስቀጣቸው ተግባር በመሆኑ፣ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ማንኛውም የወለድ ክፍያ ያለበት የብድር ውል ማዋዋል እንደሌለበት ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት በወለድ ሲያበድሩ የነበሩ ግለሰቦች በምን ዓይነት መንገድ ሊጠየቁ እንደሚችሉ አቶ ፈቃዱ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡መረጃው
የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
