አዲስ ጊዜ

227 Posts
በዋግ-ኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ ቀጥሏል።

በዋግ-ኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ ቀጥሏል።

አሸናፊ አሰበ 16/04/2016 በዋግ-ህምራ ብሔረሰብ ዞን የ2015 የክረምት ወቅት የዝናብ ስርጭት መዛባቱን ተከትሎ የተፈጠረው ድርቅ በተለይም በእንስሳት በኩል ተባብሶ መቀጠሉን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለአዲስ ጊዜ ተናግረዋል። በዞኑ ከሚገኙት 9 የገጠር ወረዳ እና 3 የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ በተለይም በሦስት ቀበሌዎች የ 2015/16 የምርት ዘመን ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን በ 3 ወረዳዎች እና በ26 ቀበሌዎች ውስጥ የከፋ ድርቅ ተከስቷል ብለዋል። ከ 171ሺ በላይ እንስሳት ወደ ምስራቅ በለሳ እና ሌሎች የሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች እንዲሻገሩ ተደርጓል ያሉት ሃላፊው እስከ ታህሳስ ወር ባለው መረጃ 10ሺ በላይ እንስሳት ለሞት መዳረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል። በመኸር…
ተጨማሪ ያንብቡ
“…..በወልቂጤ ተከስቶ በነበረው ሁከት ማጣራት በማድረግ ተጎጂዎች ሊካሱ ይገባል።” ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

“…..በወልቂጤ ተከስቶ በነበረው ሁከት ማጣራት በማድረግ ተጎጂዎች ሊካሱ ይገባል።” ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

16/04/2016 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ባወጣው ሪፖርት እንዳስነበበው ከጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስና ያስከተለውን ጉዳት ከአካባቢው ነዋሪዎች በቀረበለት አቤቱታ መነሻነት ከጥቅምት 20 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት ምርመራ ማከናወኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ ከተጎጂዎች እና ምስክሮች ጋር 22 ቃለ-መጠይቆች አድርጓል ያለው ሪፖርቱ ከጉራጌ ዞን፣ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እና ከቀቤና ልዩ ወረዳ የሥራ ኃላፊዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል። ዘረፋ እና ውድመት የደረሰባቸው እና የግል እና የመንግሥት ተቋማትን ኮሚሽኑ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን ተጎጂዎች ሕክምና ካገኙባቸው የሕክምና ተቋማት…
ተጨማሪ ያንብቡ
በኦሞ ወንዝ መሙላት ምክንያት የተፈጠረው ጎርፍ 123ሺ ሄክታር የግጦሽ መሬት ሸፍኗል ።

በኦሞ ወንዝ መሙላት ምክንያት የተፈጠረው ጎርፍ 123ሺ ሄክታር የግጦሽ መሬት ሸፍኗል ።

አሸናፊ አሰበ 16/04/2016 በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ ከሚገባው በላይ በመሙላቱ ምክንያት በተፈጠረው ጎርፍ 79,828 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በ 12 መጠለያ ጣብያዎች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ እና ጎርፋም  123ሺ ሄክታር የግጦሽ መሬት ላይ ተኝቶ እንዳለ የወረዳው የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሰኢድ ለአዲስ ጊዜ ገለጹ። በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ 6 አርብቶ አደር ወረዳ እና አንድ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሲሆን 16ሺ እማውራ እና አባውራ(ቤተሰቦች) በጎርፉ ምክንያት መፈናቀላቸው ተሰምቷል ። ከ 2012 ዓ.ም አንስቶ በተደጋጋሚ በወረዳው እየተከሰተ ያለው ጎርፉ በከፍተኛ ሁኔታ ነዋሪዎችን ይማረረ ሲሆን ተፈናቃዮች በአሁኑ ሰዓት ተጠልለው በሚገኙበት መጠለያ ጣብያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ገና-ተዋህዶ ኤክስፖ ያጋጠመው ምንድነው?

ገና-ተዋህዶ ኤክስፖ ያጋጠመው ምንድነው?

አሸናፊ አሰበ 16/04/0216 ማርኮናል ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እና ከታህሳስ 11-27/2016 ዓ.ም በጃንሜዳ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ገና ተዋህዶ ኤክስፖ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላም እና ጸጥታ ማስከበር ቢሮ ፍቃድ ባለመስጠቱ ምክንያት መካሄድ እንዳልቻለ የማርኮናል ኤቨንት ኦርጋናይዘር ባለቤት ኤፍሬም አደፍርስ ለአዲስ ጊዜ ተናግረዋል። ይጀምራል ተብሎ ማስታወቂያ ከተነገረበት ቀን በ አምስት ቀናት የዘገየው ኤክስፖው እስካሁን ፍቃድ የሚሰጠው አካል ባለማግኘቱ የሚካሄድበት ቀን አልታወቀም። የሚካሄድበት ቀን ከመድረሱ ቀደም ብሎ ወደ ጽ/ቤቱ ፍቃድ ለማግኘት ብዙ ተመላልሰናል ያሉት አዘጋጆቹ ዛሬ ነገ ስንባል ቀኑ በመድረሱ ምክንያት ነጋዴዎች ወደ ጃንሜዳ እንዲገቡ ፈቅደን ነበር ያሉ ሲሆን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢዜማ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በብቃት መመዘኛ ፈተና ላይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ።

ኢዜማ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በብቃት መመዘኛ ፈተና ላይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ።

16/04/2016 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ(ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ  ብልሹ አሰራር በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይባቸው እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መጓደል ያለባቸው ሲል የጠቀሳቸው 16 ተቋማት ላይ ከ 14,000 በላይ ሠራተኞች ለፈተና ለማስቀመጥ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በመርኅ ደረጃ የሚበረታታ ተግባር ነው ብሎ ፓርቲው እንደሚያምን ገልጿል። በእነዚህ አስተዳደር መ/ቤቶች የተገልጋይን ስም እንኳ በቅጡ በሠነዶች ላይ ማስፈር የማይችሉ፣ ፈጣን አገልግሎት እንዲሠጡ ታስበው አገልግሎት ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም የማይችሉ፣ ከሥነምግባር ያፈነገጡ እና በሌብነት የተተበተቡ ሠራተኞችን መመልከት የተለመደ ሆኗል ያለው ፓርቲው ሌላው ቀርቶ አንድ ዜጋ በነፃነት ለመንቀሣቀስ የሚያስፈልገውን የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት እንኳ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢዜማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የህዝብ ተወካይ እና የፓርቲ አባሌ በአስቸኳይ ይፈቱ ሲል ጠየቀ

ኢዜማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የህዝብ ተወካይ እና የፓርቲ አባሌ በአስቸኳይ ይፈቱ ሲል ጠየቀ

12/04/16 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመግለጫው "በ2013 ዓ.ም በተደረገው ስድስተኛ ሀገር አቀፉ ምርጫ ካሸነፈባቸው የምርጫ ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው ዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል በሚገኙ አባላት ላይ በተለያየ ጊዜ ልዩ ልዩ ጥቃቶች እየደረሱ እንደሆነ ጥቅምት 20/2016 እና ታህሣሥ 05/2016 ዓ.ም ባወጣናቸው መግለጫዎች ማሳወቃችን ይታወቃል ።“ ብሏል፡፡ ከላይ በጠቀስናቸው መግለጫዎቻችን እንደገለፅነው በጋሞ ዞን የሚገኙ የመንግሥት አካላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚፈጽሟቸውን ተግባራቶች እንዲያቆሙ፣ በእነዚህ ድርጊቶች የተሣተፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ያለአግባብ የታሠሩ አባሎቻችን እንዲፈቱ እና አስፈላጊው ካሣ እንዲፈጸምላቸው በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም የጋሞ ዞን አመራሮች ከዚህ ተግባራቸው ለመቆጠብ ምንም አይነት ተነሣሽነት የሌላቸው መሆኑን እና ህገወጥ ድርጊቱም ተባብሶ መቀጠሉን አረጋግጠናል ።…
ተጨማሪ ያንብቡ
<<ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የመለየት ስራ በቅርቡ ይጀመራል፡፡>>

<<ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የመለየት ስራ በቅርቡ ይጀመራል፡፡>>

12/04/2016 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በፅህፈት ቤቱ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ በ327 ወረዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ መነሳት አለባቸው ያሏቸውን አጀንዳዎች የሚለዩ ተሳታፊዎች መለየታቸውን አስታውቋል። ከትግራይና ከአማራ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ለምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የሚለዩና በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ ተወካዮች መምረጣቸውን የጠቀሱት ኃላፊው መዲናዋን ጨምሮ የተሳታፊዎች ልየታ በተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች ለምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ለመለየት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። በተለያዩ የአገሪቱ 700 ወረዳዎች ላይ የተሳታፊዎች ልየታ እየተከናወነ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ 327 ወረዳዎች የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮችን መመርጣቸውን ጠቁመዋል። በአማራ እና በትግራይ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ

የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ

የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ሲል የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ እንደ አገልግሎቱ መረጃ የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት 28.3 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች(food items) 30 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) 26 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል፡፡ በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በጥቅምት ወር ከነበረበት 29.2 በመቶ ወደ 28.3 በመቶ መቀነሱን መረጃው ያሳያል ማለቱን ከአገልግሎቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክተናል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
4ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሸ ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ

4ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሸ ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ

10/04/16 አሸናፊ አሰበ ኢትዮጵያ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ያለውን ልዩነት በመፍታት ሁሉን ተጠቃሚ ያደረገ ስምምነት ለመድረስ ፍላጎት ብታሳይም ግብጽ በግድቡ ላይ እስካኹን በተደረጉት ድርድሮች ባራመደችው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ ቀርቷል ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገለጸ። በግድቡ የውሃ አሞላል ላይ እና በግድቡ አስተዳደር ላይ ኢትዮጵያ ለድርድር የተቀመጠችው ከሀገራቱ ጋር መተማመን ማስፈን እንጂ የሀገሪቱን በአባይ ውሃ ላይ የመጠቀም እና የመልማት መብት ለመገደብ አይደለም ሲል አቋሙን ያንጸባረቀው መግለጫው ኢትዮጵያ አሁንም በግልጽ ማስቀመጥ የምትፈልገው ዋነኛ ጉዳይ የአሁኑን እና የቀጣዩን የሀገሪቱን ትውልድ ተጠቃሚ በሚያደርግ እና የእኩልነትና ምክንያታዊነት መርሆችን ባከበረ አኳኋን የወንዙን ውሃ መጠቀሟን ትቀጥላለች ብሏል። አራተኛው…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር እንዲነጋገር ጥሪ ቀረበ።

መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር እንዲነጋገር ጥሪ ቀረበ።

10/04/2016 ለዓለም አሰፋ መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር ይነጋገር ሲል ክራይሲስ ግሩፕ ጥሪ አቀረበ። በምዕራብ ሀገራት ባሉ ፖሊሲ አውጭዎች ተደማጭነት  ያለው የሀሳብ አመንጭ ተቋም ክራይሲስ ግሩፕ የአማራ ክልል ግጭት በአፋጣኝ መፍትሔ የማያገኝ ከሆነ ለሀገሪቷ አደገኛ ይሆናል ብሏል። ተቋሙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ነፍጥ ካነገቡ የክልሉ ታጣቂዎች ጋር እንዲደራደሩ ምክር ለግሷል። መቀመጫውን በቤልጂየሟ መዲና ብራስልስ ያደረገዉ መንግስታዊ ያልሆነዉ ይህ ተቋም በዓለም ዙርያ ያሉ ቀውሶችን በመመርመር ትንታኔዎችን ያቀርባል፤ በመንግስታት ፖሊሲ አርቃቂዎች፥ በምሁራን እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ትንታኔዎቹ ተደማጭነት አላቸው። ድርጅቱ የአማራ ክልል ግጭትን አስመልክቶ ባወጣዉ  መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሦስቱ ክልሎች በኦሮሚያ፥ በትግራይ እና አሁን ደግሞ በአማራ መንግስትን የሚቃወሙ…
ተጨማሪ ያንብቡ