12/04/16
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመግለጫው “በ2013 ዓ.ም በተደረገው ስድስተኛ ሀገር አቀፉ ምርጫ ካሸነፈባቸው የምርጫ ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው ዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል በሚገኙ አባላት ላይ በተለያየ ጊዜ ልዩ ልዩ ጥቃቶች እየደረሱ እንደሆነ ጥቅምት 20/2016 እና ታህሣሥ 05/2016 ዓ.ም ባወጣናቸው መግለጫዎች ማሳወቃችን ይታወቃል ።“ ብሏል፡፡
ከላይ በጠቀስናቸው መግለጫዎቻችን እንደገለፅነው በጋሞ ዞን የሚገኙ የመንግሥት አካላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚፈጽሟቸውን ተግባራቶች እንዲያቆሙ፣ በእነዚህ ድርጊቶች የተሣተፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ያለአግባብ የታሠሩ አባሎቻችን እንዲፈቱ እና አስፈላጊው ካሣ እንዲፈጸምላቸው በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም የጋሞ ዞን አመራሮች ከዚህ ተግባራቸው ለመቆጠብ ምንም አይነት ተነሣሽነት የሌላቸው መሆኑን እና ህገወጥ ድርጊቱም ተባብሶ መቀጠሉን አረጋግጠናል ።
ይህ ህገወጥ ድርጊት ቀጥሎ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰብ እና ህዝቦች ክልል የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ተወካይ እና የኢዜማ አባል የሆኑትን አቶ አማንያስ ጉሹና በኤፌድሪ ሕገመንግስቱ አንቀጽ 54(6) የተጠቅሰውን ድንጋጌ ተላልፈው ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ባልተያዘበት እና ያለመከሰስ መብታቸው በም/ቤቱ ባልተነሳበት ሁኔታ ከታህሳስ 09/2016 ዓ.ም. ጀምሮ በጋሞ ዞን አስተዳደር ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውለው በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ የሚገኙ ሲሆን ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን አረጋግጠናል።
ይህ አይነቱ በሕገመንግሥቱ በግልጽ የተጠቀሰ መብት ሲጣስ የመጀመርያው አለመሆኑን ከዚህ ቀደም በዚሁ ክልል በተመሣሣይ ያለመከሰስ መብታቸው ባልተነሣበት ሁኔታ በቁጥጥር ሥር የዋሉ አባላችንን አስመልከቶ ድርጊቱ ህገመንግስታዊ ጥሰት መሆኑን “የሚወሰዱ እርምጃዎች ሕግና ሕግን ብቻ ተከትለው ሊሆን እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተን ለማሳሰብ እንወዳለን” ሲል ሕዳር 18/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ማሣወቁ የሚታወስ ነው።
መንግሥት በአባሎቻችንም ሆነ በዜጎች ላይ የሚፈጽማቸው የትኛውም ሕግን መሠረት ያላደረጉ ነገር ግን መንግሥት ሕግ ማስከበሮች ብሎ በሚጠራቸው ህገወጥ ተግባራቶች ምክንያት ያለውን ተዓማኒነት እንዲያጣ የሚያደርግ እና ፍጹም ገፊ የሆኑ ድርጊቶች መሆናቸውን ሊነገዘብ ይገባል ብሎም ለሚመጣውም ችግር ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል።
ፓርቲያችን በግልጽ ካስቀመጣቸው እሴቶቹ አንዱ “ተጠያቂነት” እንደሆነ ይታወቃል፤ ተጠያቂነት መኖር ላይ ምንም አይነት ለድርድር የማይቀርብ የማያወላዳ አቋም ቢኖረውም ይህ ተጠያቂነት ግን ከላይ በተጠቀሠው መልኩ ተጠያቂነት እንዲሰፍን አስቻይ ከሆነው ሀገሪቱ ከምትተዳደርበት ሕገመንግስትም ሆነ ሌሎች ገዢ ሕጎች ውጪ ሲሆን በፍፁም የማንቀበለው መሆኑን በተደጋጋሚ የገለጽን ሲሆን አሁንም በድጋሜ ለማሣወቅ እንወዳለን።
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በዛይሴ ልዮ ምርጫ ክልል እየተባባሰ የመጣው. በአባሎቻችን የሚፈፀመው ህገወጥ ድርጊት እና ግጭቶች ወደከፋ ሆኔታ ከማምራታቸው በፊት መፍትሔ ሊበጅላቸው ይገባል እንላለን። በመሆኑም አባላችን እና የደቡብ ኢትዮጵያ ም/ቤት ተወካይ የሆኑትን አቶ አማንያስ ጉሹና በአስቸኳይ እንዲፈቱ በአፅንኦት እንጠይቃለን” ብሏል ፓርቲው
በተለያዩ የአገሪቱ 700 ወረዳዎች ላይ የተሳታፊዎች ልየታ እየተከናወነ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ 327 ወረዳዎች የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮችን መመርጣቸውን ጠቁመዋል።
በአማራ እና በትግራይ ክልል ተሳታፊዎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ያነሱት አቶ ጥበቡ የተሳታፊዎች ልየታ ባልተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች በቀጣዮቹ ሳምንታት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል ፡፡
