“የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም” በሚል መሪ ሃሳብ “ማስታወሻ ሁለት ተካሄደ

“የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም” በሚል መሪ ሃሳብ “ማስታወሻ ኹለት” ታህሳስ 14 ቀን 2016 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተካሂዷል።

ማስታወሻ መልቲሚዲያ እና ፕሮሞሽን ጋዜጠኝነት በራሱ ማንነት እንዲሄድ፣ ልምድ እንዲጎለብትና የሀሳብ ልውውጥ እንዲደረግ በተከታታይ መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ይታወቃል።

በማስታወሻ መልቲሚዲያና ፕሮሞሽን የተዘጋጀው ይኸው መድረክ፤ ደራሲና ተርጓሚ ሣሕለስላሴ ብርሃነማርያም እና ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃን(ማንን ምን እንጠይቅልዎ) በዕለቱ የማመስገን እና የመዘከር ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዕለቱ ቀደምቶቹን ከማመስገን ባሻገር የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች ቀርበዋል።

“ማስታወሻ አንድ” ከዚህ ቀደም ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላን ማመስገንና መዘከሩ የሚታወስ ነው።