16/04/2016
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ(ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ብልሹ አሰራር በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይባቸው እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መጓደል ያለባቸው ሲል የጠቀሳቸው 16 ተቋማት ላይ ከ 14,000 በላይ ሠራተኞች ለፈተና ለማስቀመጥ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በመርኅ ደረጃ የሚበረታታ ተግባር ነው ብሎ ፓርቲው እንደሚያምን ገልጿል።
በእነዚህ አስተዳደር መ/ቤቶች የተገልጋይን ስም እንኳ በቅጡ በሠነዶች ላይ ማስፈር የማይችሉ፣ ፈጣን አገልግሎት እንዲሠጡ ታስበው አገልግሎት ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም የማይችሉ፣ ከሥነምግባር ያፈነገጡ እና በሌብነት የተተበተቡ ሠራተኞችን መመልከት የተለመደ ሆኗል ያለው ፓርቲው ሌላው ቀርቶ አንድ ዜጋ በነፃነት ለመንቀሣቀስ የሚያስፈልገውን የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት እንኳ ሲጉላላ እና እጅ መንሻ ሲጠየቅ ይስተዋላል ሲል በመግለጫው አስነብቧል።
ሆኖም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው እነዚህን አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች የሚመሩት የገዢው ፓርቲ አመራሮችም ሆነ ገዢው ፓርቲ እንደተቋም ለብሄርተኝነት ባላቸው የተዛባ ውግንና በተደጋጋሚ በሚያደርጓቸው አግላይ የአደባባይ ንግግሮች እና አሠራሮች ምክንያት እያንዳንዱ በነዚህ አካላት የሚደረግ እንቅስቃሴ እና ውሳኔ በማኅበረሰቡ በጥርጣሬ የሚታይ እንዲሆን አድርጎታል ብሏል በመግለጫው፡፡
አስተዳደሩ ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት በጥርጣሬ እንዲታዩ መሆናቸውን መገንዘብ ይገባቸዋል ያለው ፓርቲው ተገቢውን ማብራርያ በወቅቱ መስጠት ዜጎችን ከስጋትና እና ውዥንብር ያድናል ሲል አሳስቧል።
ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከታች የተቀመጠውን ሊ

