የጣና ሃይቅ እንቦጭ መታረም ከነበረበት ጊዜ በአራት ወራት መዘግየቱ ተነግሯል
አሸናፊ አሰበ 17/04/2016 የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በአማራ ክልል ውስጥ በተከሰተው የሠላም እጦት ምክንያት የህዳሴ ግድቡ መጋቢና የከተማው እስትንፋስ የሆነው ጣና ሃይቅ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሃይቁን ከዚህ ተግዳሮት ለመታደግ የሚደረገው ጥረት በየጊዜው በክልሉ የሚፈጠሩ የሠላም ችግሮች እየተደናቀፈ ይገኛል ያለው ቢሮው በዚህ የተነሳ የእምቦጭ አረምን ለማጥፋት ሲደረግ የነበረው ጥረት መስተጓጎል ገጥሞታል ብሏል። ቀደም ሲል በመንግስት ግዥና በተለያዩ ድጋፎች የመጡት የአረም ማስወገጃ መሳሪያዎች አፈር እየበላቸውና ተበላሽተው ከጥቅም ውጭ እየሆኑ እንደሆነ ቢሮው ገልጿል። ይህንን ተግባር በተልዕኮነት ተቀብሎ የሚሰራው ኤጄንሲም በሠላም ችግር ምክንያት ተንቀሳቅሶ ለመስራት ባለመቻሉ በተለያየ ዘዴ አረሙን በተጨባጭ ለማስወገድ ተጀምረው የነበሩ…
