ባህር ዳር ዩንቨርስቲ የክልሉ ሰላም በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ መደበኛ ተማሪዎችን አስገብቶ ለማስተማር አያስችልም አለ።
አሸናፊ አሰበ 16/04/2016 በአማራ ክልል የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለነባር እንዲሁም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቻቸው ጥሪ ሳያደርጉ አራት ወራት ተቆጥረዋል። ተማሪዎችም ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድባቸውና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጉትጎታ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ትምህርት ሚኒስቴር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አስሩም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተው ትምህርት እንዲያስቀጥሉ እንደተነገራቸው እና ተቋማቱም በቅርቡ ጥሪ ለማድረግ መስማማታቸውን ይናገራል። ይህንንም ተከትሎ አዲስ ጊዜ ትምህርት መቼ ለመጀመር እንዳቀዱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ግርማው አሸብርን ጠይቃለች። አንደ አቶ ግርማ ገለጻ ዩኒቨርሲቲው በማንኛውም ሰዓት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ መሆኑንና በአሁኑ ሰዓትም በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ የድሕረ ምረቃ ተማሪዎች…
