በዋግ-ኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ ቀጥሏል።
አሸናፊ አሰበ 16/04/2016 በዋግ-ህምራ ብሔረሰብ ዞን የ2015 የክረምት ወቅት የዝናብ ስርጭት መዛባቱን ተከትሎ የተፈጠረው ድርቅ በተለይም በእንስሳት በኩል ተባብሶ መቀጠሉን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለአዲስ ጊዜ ተናግረዋል። በዞኑ ከሚገኙት 9 የገጠር ወረዳ እና 3 የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ በተለይም በሦስት ቀበሌዎች የ 2015/16 የምርት ዘመን ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን በ 3 ወረዳዎች እና በ26 ቀበሌዎች ውስጥ የከፋ ድርቅ ተከስቷል ብለዋል። ከ 171ሺ በላይ እንስሳት ወደ ምስራቅ በለሳ እና ሌሎች የሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች እንዲሻገሩ ተደርጓል ያሉት ሃላፊው እስከ ታህሳስ ወር ባለው መረጃ 10ሺ በላይ እንስሳት ለሞት መዳረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል። በመኸር…
