ሂውማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አላከበረችም ሲል ተቸ።
ሂውማን ራይትስ ዎች አዲስ ባወጣው የዓለም የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የፕሪቶሪያውን ስምምነት እና የአማራ ክልል ግጭትን የዳሰሰ ሲሆን በኢትዮጵያ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተጠያቂነት እንዲሰፍንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ወደሚያስችሉ ዓለማቀፋዊ ርምጃዎች አላመራም በማለት ተችቷል። በአማራና ትግራይ ክልሎች በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ሌሎች ጥሰቶች እስከአሁንም ቀጥለዋል ያለው ድርጅቱ፣ አውሮፓ ኅብረትና ሌሎች ምዕራባዊያን አገራት ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግንኙነታቸውን እንደገና ጀምረዋል በማለት ወቅሷል። የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይደርስ እንደሚያደናቅፉና በአማራ ክልልም ውጊያ፣ የቴሌኮምንኬሽን መቋረጥና በረድዔት ሠራተኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለዕርዳታ ሥርጭት እንቅፋት እንደሆኑ ሪፖርቱ ጠቅሷል። በሚያዝያ ወር የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እየተባባሰ የመጣው የፌደራል መንግስት የክልሉን…
