4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ተገለጸ

30/04/2016

የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን ወቅታዊ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተመለከተ በሰጡት የጋራ መግለጫ አውጥተዋልሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ገልጸዋል።

በመግለጫቸውም በአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ ፣ደቡብ ፣ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎች ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደስፈልጋቸው አስታውቋል።

በታህሳስ ወር አጋማሽ እንደገና በተጀመረው የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የሌሎች አጋር አካላት እገዛ በአማራ ፤በትግራይ፣ በሶማሌና በአፋር ክልሎች በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች ወደ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።

የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት የቅድሚያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ በጥር ወርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ለጋሽ አካላትም ይሄንኑ እንስቃሴ ለማገዝ ትኩረት እንዲሰጡ በመግለጫው ጥሪ  አቅርቧል። ወቅቱን የጠበቀ ምላሽ በገንዘብ ድጋፍና በሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑም ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ተደራሽ ለማድረግም የተቀናጀ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት አስፈላጊ መሆኑ በመግለጫው ጠቅሶ እንደ ወባ፣ ኩፍኝና ኮሌራ ያሉ በሽታዎች መከሰትን ጨምሮ በቀንድ ከብቶች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

መንግስትና የረድኤት ድርጅቶች ሰብዓዊ እርዳታ በማድረስ በኩል ያላቸውን ልምድና የተጠናከረ የባለሙያ ስብስብ ለዚሁ ተግባር ለማዋል ዝግጁ መሆናቸውም መግለጫው አመልክቷል።