የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነትን “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ

01/05/2016

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን  መግባቢያ ሰነድ “ያለልዩነት” የምንደግፍ መሆናችንን እናረጋግጣለን ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በመግለጫውም ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እና እድሎችን በዝርዝር በመምከር ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናቸውን ለመወጣት ፓርቲዎቹ ዝግጁ መሆናቸውን የጋራ ምክር ቤቱ ተአስታውቋል።ሶማሊያዊያን ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን ስምምነት በመቃወም “ዋን ሚሊዮን ማርች” የተሰኘ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊንዱ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የገቡትን ስምምነት እየተቃወሙ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ስምምነትም የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር አይኖርም፤ የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም በማለት መግለጹ ይታወቃል። ሶማሊላንድ ስምምነቱን በሚቃወሙ አካላትና ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።

የተባበሩት መንግስታት የባህር በር ህግ አንቀጽ 69 የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በአካባቢው ያለውን የባህር በር የመጠቀምና የመሸጋገር አለም አቀፍ መብት እንዳላቸው ቢደነግግም፤ አሁንም በርካቶች ተቃውሟቸውን ቅሬታቸውና ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።