30/04/16
ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በኢንተርኔት መዘጋት ብቻ ከ1.59 ቢልየን ዶላር በላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰባት ‘ቶፕ10ቪፒኤን’ የተሰኘ ድረ ገፅ ይፋ አደረገ። ከሩሲያ በመቀጠልም ከዓለም ከፍተኛ ኪሳራ በማስተናገድ ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች።
የኢንተርኔት መዘጋት በዓለም ዙሪያ ያደረሰውን ኪሳራ የተመለከተው የ2023 ዓመት ሪፖርት እንደሚያሳየው ለ15 ሺህ ሰዓታት ገደማ በኢትዮጵያ ኢንተርኔት የተቋረጠ ሲሆን ይህም 29.8 ሚልየን ህዝብ ከኢንተርኔት ጋር ተለያይተው የቆዩበት ዓመት ሆኗል።
የኢንተርኔት መዘጋቶች በሀገሪቱ በነበሩበት ወቅትም በዋነኛነት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች ተጥሰዋል ሲል ድረ ገፁ አስታውቋል።
የ2023 ዓመት ሪፖርቱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ኢትዮጵያ በ2022 178 ሚልየን ዶላር ገደማ ያጣች ሲሆን ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ነበር።
የብሔራዊ ፈተናዎች እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች በኢትዮጵያ ዋነኛ የኢንተርኔት መዘጋት ምክንያቶች ናቸው።
