“ያደጉት ሃገራት የገቡትን ቃል እንደሚከውኑት ከአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤው ይጠበቃል” አቶ ነመራ ገበየሁ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ130 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት 28ተኛው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከህዳር 20 - ታህሳስ 2 በዱባይ እንደሚካሄድ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ነመራ ገበየሁ ገለጹ። ጉባኤው በዓመት አንድ ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪነት የሚዘጋጅ ሲሆን ኢትዮጵያን በሚወክለው ልኡክም ዝግጅት እንደተደረገ ተነግሯል። በአጠቃላይ ለ12 ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ከህዳር 20 - 21 የሃገራት መሪዎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ሲሆን መሪዎችም የሀገራቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲዎችን እንደሚያስተዋውቁ እና በመሪ ደረጃ ሊነሱ የሚገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ፓሊሲዎችን እንደሚያስተዋውቁ ይጠበቃል። በቀሪው የጉባኤው ወቅትም መሪዎች በሚያስቀምጡት መመሪያ መሰረት ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል። በጉባኤው እ.አ.አ በ2015 ተደርጎ በነበረው የፓሪሱ የአየር…
