በሀዲያ ዞን ባዳዋቾ ክላስተር  ትምህርት ባለመጀመሩ ተማሪዎች  ሰላማዊ  ሰልፍ አካሄዱ ።

የመምህራን ደመወዝ ከሀምሌ ወር ጀምሮ ባለመከፈሉ ምክንያት፤ በጉምቦረ ወረዳ ፣በምዕራብ ሶሮ ወረዳ ፣ በግቤ ወረዳ፣ በምስራቅ በደዋቾ ፣ምዕራብ በደዋቾ፣ በሆማቾ ና ሾኔ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በአማካ ወረዳ የትምህርት ስራ ሙሉ በሙሉ ቆሞ ይገኛል።

ነገር ግን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት መፍትሔ ከመንግስት ባለመሰጠቱ ምክንያት ተማሪዎች  ቅሬታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።

የተማሪዎች ወላጆችና መምህራን ይህ በሀድያ ዞን ሁለት  አይነት መንግስት መኖሩን ያመለክታል ያሉ ሲሆን  ሆን ተብሎ  ከለይ በተጠቀሱ ወረዳዎች ፤ ከተማ  አስተዳደሩ  የትዉልድ  ክፍተት እንዲፈጠር ያደረገ ሴራ ሲሉ መንግስትን ተችተዋል። 

ትምህርት  በሌሞ በሆሳዕና ከተማ  እና በፎንቆ አልቆመም፤  የመምህራን ደመወዝ እዛ እየተከፈለ  እኛ ጋር የለም የሚሉት መምህራን ፤ይህም ከበጀት እጥረት ሳይሆን ሌላ አላማ ያለመ መሆኑን  ግልጽ ማሳያ ነው ብለዋል ።

 በዚህም ምክንያት በጉምቦረ ፣ግቤ፣ ሆማቾ፣ ምዕራብ ሶሮ ፣ ምዕራብ በደዋቾ ምስራቅ በደዋቾ አማከ እና ሾኔ ከተማ ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።