ህዳር 30 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
ህዳር 19/2016 "ጦርነት ይቁም፣ ሰላም ይስፈን፣ መከላከያ ሰራዊቱ በአስቸኳይ ወደካምፕ ይግባ" በሚል መሪ ቃል ለህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱን አዲስ ጊዜ ማረጋገጥ ችላለች፡፡ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ እና የአደባባይ ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የገባው የሰልፍ ጥሪ ደብዳቤ እንደሚያብራራው፣ ሰልፉ ከተዘጋጀበት ዋንኛ ዓላማዎች መካከል ቀዳሚው "የመከላከያ ሰራዊቱ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ውስጥ በመግባት ደም አፋሳሽ ተግባር ውስጥ በመሆኑ ከተሰጠው የሀገር ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሚና ውጭ ከሚያደርገው ዘመቻ በመቆጠብ ወደጠቅላይ ጦር ሰፈሩ እንዲገባ የሚጠይቅ" ነው፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች በደብዳቤው ላይ እንደገለጹት የጥሪው ዓላማዎች መከላከያ ሰራዊቱን የሚመለከቱ ብቻ ሳይሆኑ፣ "በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ…
