አዲስ ጊዜ

228 Posts
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነትን “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነትን “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ

01/05/2016 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን  መግባቢያ ሰነድ “ያለልዩነት” የምንደግፍ መሆናችንን እናረጋግጣለን ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመግለጫውም ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እና እድሎችን በዝርዝር በመምከር ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናቸውን ለመወጣት ፓርቲዎቹ ዝግጁ መሆናቸውን የጋራ ምክር ቤቱ ተአስታውቋል።ሶማሊያዊያን ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን ስምምነት በመቃወም “ዋን ሚሊዮን ማርች” የተሰኘ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊንዱ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የገቡትን ስምምነት እየተቃወሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ስምምነትም የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር አይኖርም፤ የተጣሰ ሕግና የተሰበረ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመወያየት ሃሳብ እንዳለው አስታወቀ

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመወያየት ሃሳብ እንዳለው አስታወቀ

ከአባላት መታሰርና የጽህፈት ቤት መዘጋት ጋር በተያያዘ ክስ የሚያቀርበው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ በሰላማዊ የድርድር ማእቀፍ ውስጥ ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡ ኦፌኮን ጨምሮ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ መጻኢ እድል ላይ የሚያካሂዱት የተበጣጠሰ የሰላማዊ ትግል አካሄድ አገሪቱን ከማዳን ይልቅ ወደባሰ አዘቅት እየከተታት ነው ያሉት የኦፌኮ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ሁሉን አቀፍ በሆኑ የውይይትና የድርድር ማእቀፍ ውስጥ መወያየት ለአገር የሚበጅ ነው ብለዋል፡፡ ኦፌኮ ላለፉት ዓመታት በሰላዊ የትግል መስመር የፖለቲካ ተሳትፎ ሲያደርግ የነበረና አሁንም እያደረገ ነው ያሉት ሃላፊው ነገር ግን ለብቻ በሚደረጉ ትግሎች ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ፓርቲው ግንዛቤን…
ተጨማሪ ያንብቡ
በሶማሊላንድ ሃርጌሳ ጸረ ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው ተነገረ።

በሶማሊላንድ ሃርጌሳ ጸረ ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው ተነገረ።

01/05/2016 ከኢትዮጵያ ጋር የወደብ ኪራይ ስምምነት ውል የገባችው ሶማሊላንድ ስምምነቱን በሚቃወሙ ሰዎች በሶማሊኛ ቋንቋ “ኢትዮጵያዊ ላይ በተገኘበት እርምጃ ይወሰድበት” የሚል በራሪ ጽሑፍ በሐርጌሳ ከተማ እየተበተነ መሆኑ ተነግሯል። በዚህም ምክንያት በሶማሊላንድ ለሚገኙ ከ 40 ሺ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በጣም አሳሳቢ ወቅት ሆኗል። በተለይም የኦሮሞ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ትኩረት በማድረግ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ለማድረስ፣ ንብረት ለመዝረፍ፣ እና ቤታቸውን በእሳት ለማቃጠል ሙከራ ተደርጓል  ተብሏል። በሶማሊላንድ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ በሆነችው በቦርኦ ከተማ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ጉዳት መድረሱን እና ንብረታቸው መዘረፉ ተነግሯል። በሶማሊላንድ የስደተኞች ተወካይ እንደሚሉት ስደተኛ ነዋሪዎች ስጋታቸውን ለሶማሊላንድ ባለስልጣናት ካሳወቁ በኋላ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከመፅፍቱ ጋር የተቀበረው ወጣት

ከመፅፍቱ ጋር የተቀበረው ወጣት

አሸናፊ አሰበ 01/05/2016 በ 1926 ዓም የየተገነባው  በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ አካባቢ የሚገኘው በተለምዶ ሎምባርዲያ ተብሎ የሚጠራው ህንጻ መጽሐፍን ከነ መጽሐፍ አዟሪው በዕለተ አርብ ታህሳስ 26/2026 ከምሽቱ 1 ሰዓት  ወደ ፍርስራሽነት ተቐይሯል። ጌትነት ክፍሌ ይባላል መጽሐፍትን እያዞረ በመሸጥ የሚተዳደር ለፍቶ አዳሪ የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው። ጌትነት ሎምባርዲያን በአካባቢው ተመሳሳይ ስራ በመስራት ከሚተዳደሩ መጻህፍት ሻጮች ጋር ለመጻህፍት ማሳደሪያነት በኪራይ ይገለገሉበት ነበር። ታዲያ በተጠቀሰው ቀን  ሎምባርዲያን ለማፍረስ የተንቀሳቀሰ አፍራሽ ግብረ ኃይል በምሽት መጣ ፡፡ጌትነት እና ሌሎች እቃዎቻቸውን እና በውስጥ የነበሩ መጽሐፍቶችን ለማውጣት ወደ መጋዘኑ ገቡ ፡፡ አፍራሽ ግብረ ሃይሎቹግን እነ ጌትነት እስኪወጡ  አልታገሱትም…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ በ2023 ዓመት በኢንተርኔት መዘጋት ከ1.5 ቢልየን ዶላር በላይ ማጣቷ ተገለፀ

ኢትዮጵያ በ2023 ዓመት በኢንተርኔት መዘጋት ከ1.5 ቢልየን ዶላር በላይ ማጣቷ ተገለፀ

30/04/16 ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በኢንተርኔት መዘጋት ብቻ ከ1.59 ቢልየን ዶላር በላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰባት 'ቶፕ10ቪፒኤን' የተሰኘ ድረ ገፅ ይፋ አደረገ። ከሩሲያ በመቀጠልም ከዓለም ከፍተኛ ኪሳራ በማስተናገድ ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች። የኢንተርኔት መዘጋት በዓለም ዙሪያ ያደረሰውን ኪሳራ የተመለከተው የ2023 ዓመት ሪፖርት እንደሚያሳየው ለ15 ሺህ ሰዓታት ገደማ በኢትዮጵያ ኢንተርኔት የተቋረጠ ሲሆን ይህም 29.8 ሚልየን ህዝብ ከኢንተርኔት ጋር ተለያይተው የቆዩበት ዓመት ሆኗል። የኢንተርኔት መዘጋቶች በሀገሪቱ በነበሩበት ወቅትም በዋነኛነት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች ተጥሰዋል ሲል ድረ ገፁ አስታውቋል። የ2023 ዓመት ሪፖርቱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ኢትዮጵያ በ2022 178 ሚልየን ዶላር ገደማ ያጣች ሲሆን ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ነበር።…
ተጨማሪ ያንብቡ
4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ተገለጸ

4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ተገለጸ

30/04/2016 የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን ወቅታዊ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተመለከተ በሰጡት የጋራ መግለጫ አውጥተዋልሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ገልጸዋል። በመግለጫቸውም በአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ ፣ደቡብ ፣ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎች ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደስፈልጋቸው አስታውቋል። በታህሳስ ወር አጋማሽ እንደገና በተጀመረው የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የሌሎች አጋር አካላት እገዛ በአማራ ፤በትግራይ፣ በሶማሌና በአፋር ክልሎች በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች ወደ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት የቅድሚያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ በጥር ወርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል። ለጋሽ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢህአፓ በመቀሌ የፊታችን እሁድ ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ሰልፍ ቀርቷል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሃሰተኛ ዜና ነው ሲል አጣጣለ።

ኢህአፓ በመቀሌ የፊታችን እሁድ ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ሰልፍ ቀርቷል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሃሰተኛ ዜና ነው ሲል አጣጣለ።

አሸናፊ አሰበ 17/04/2016 ህዳር 30/2016 ዓም በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ የተከለከለው ሰልፍ የፊታችን እሁድ በመቀሌ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ሰልፋ እንደማይካሄድ ቢገልጽም ሰልፉን ከሚያስተባብሩት ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የኢህአፓ ፕሬዚዳንት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ሰልፉ እንደቀረ የሚወራውን ወሬ ፌክ ኒውስ (fake news) ሲሉ አጣጥለውታል። መቀሌ ለሚገኘው አስተባባሪ ኮሚቴ የደረሰው ደብዳቤ ሰልፋ ፍቃድ እንደተሰጠው ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ በደብዳቤ ሰልፋ መከልከሉን ያሳወቀ አካል ባለመኖሩ በታቀደለት መሰረት እሁድ ለማካሄድ ዝግጅታችንን እንደቀጠልን ነው ብለዋል እርሳቸው በመቀሌው ሰልፍ እንደሚገኙ ጥያቄ ያቀረብንላቸው ተ/ፕ ዝናቡ "እግዚአብሔር ያውቃል"  የሚል ምላሻቸውን ሰጥተውናል። የሰልፋ አስተባባሪ  አባላት አስር ሲሆኑ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ሰልፍ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሞሮኮው ንጉሥ መሃመድ 6ኛ በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2023 ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ተግባራት እና ስኬቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ሞሮኮያዊያን እና ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች አጋሩልን ብለው መልዕክት ልከውልናል፡፡ ከሞሮኮው ንጉስ መሃመድ ፕሬስ ሴክሪታሪ ዘካሪያ የተላከልንን መልዕክት ለአንባቢያን እንደወረደ አቅርበናል፡፡

የሞሮኮው ንጉሥ መሃመድ 6ኛ በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2023 ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ተግባራት እና ስኬቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ሞሮኮያዊያን እና ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች አጋሩልን ብለው መልዕክት ልከውልናል፡፡ ከሞሮኮው ንጉስ መሃመድ ፕሬስ ሴክሪታሪ ዘካሪያ የተላከልንን መልዕክት ለአንባቢያን እንደወረደ አቅርበናል፡፡

L'Engagement Visionnaire de "SA MAJESTÉ LE ROI MOHAMMED VI" pour un Maroc Prospère et Rayonnant ZAKARIYA BELLAHRACH Depuis son accession au trône de ses ancêtres bienfaiteurs, Sa Majesté le Roi Mohammed VI s'est engagé à poursuivre la construction du Maroc des institutions. Ainsi, l'État a connu, au début du XXIe siècle, un développement réel à tous les niveaux et dans divers domaines. Sa Majesté le Roi a personnellement veillé et directement supervisé d'importants chantiers qui ont fait du Maroc un leader tant au niveau régional qu'international. Ces chantiers et projets ont mobilisé la ressource humaine à…
ተጨማሪ ያንብቡ
የጣና ሃይቅ እንቦጭ መታረም ከነበረበት ጊዜ በአራት ወራት መዘግየቱ ተነግሯል

የጣና ሃይቅ እንቦጭ መታረም ከነበረበት ጊዜ በአራት ወራት መዘግየቱ ተነግሯል

አሸናፊ አሰበ 17/04/2016 የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በአማራ ክልል ውስጥ በተከሰተው የሠላም እጦት ምክንያት የህዳሴ ግድቡ መጋቢና የከተማው እስትንፋስ የሆነው ጣና ሃይቅ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።           ሃይቁን ከዚህ ተግዳሮት ለመታደግ የሚደረገው ጥረት በየጊዜው በክልሉ የሚፈጠሩ የሠላም ችግሮች እየተደናቀፈ ይገኛል ያለው ቢሮው በዚህ የተነሳ የእምቦጭ አረምን ለማጥፋት ሲደረግ የነበረው ጥረት መስተጓጎል ገጥሞታል ብሏል። ቀደም ሲል በመንግስት ግዥና በተለያዩ ድጋፎች የመጡት የአረም ማስወገጃ መሳሪያዎች አፈር እየበላቸውና ተበላሽተው ከጥቅም ውጭ እየሆኑ እንደሆነ ቢሮው ገልጿል። ይህንን ተግባር በተልዕኮነት ተቀብሎ የሚሰራው ኤጄንሲም በሠላም ችግር ምክንያት ተንቀሳቅሶ ለመስራት ባለመቻሉ በተለያየ ዘዴ አረሙን በተጨባጭ ለማስወገድ ተጀምረው የነበሩ…
ተጨማሪ ያንብቡ
“የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም” በሚል መሪ ሃሳብ “ማስታወሻ ሁለት ተካሄደ

“የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም” በሚል መሪ ሃሳብ “ማስታወሻ ሁለት ተካሄደ

"የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም" በሚል መሪ ሃሳብ "ማስታወሻ ኹለት" ታህሳስ 14 ቀን 2016 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተካሂዷል። ማስታወሻ መልቲሚዲያ እና ፕሮሞሽን ጋዜጠኝነት በራሱ ማንነት እንዲሄድ፣ ልምድ እንዲጎለብትና የሀሳብ ልውውጥ እንዲደረግ በተከታታይ መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ይታወቃል። በማስታወሻ መልቲሚዲያና ፕሮሞሽን የተዘጋጀው ይኸው መድረክ፤ ደራሲና ተርጓሚ ሣሕለስላሴ ብርሃነማርያም እና ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃን(ማንን ምን እንጠይቅልዎ) በዕለቱ የማመስገን እና የመዘከር ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በዕለቱ ቀደምቶቹን ከማመስገን ባሻገር የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች ቀርበዋል። "ማስታወሻ አንድ" ከዚህ ቀደም ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላን ማመስገንና መዘከሩ የሚታወስ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ