መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም!
እናት ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም ሲል አሳሰበ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቤተክርስቲያን ክብረ በዓላት የቤተክርስቲያኒቷን ዶግማ፣ ቀኖናና ሥርዓት ጠብቀው እንዳይከወኑ የሚያደርጉ መንግሥታዊ ጫናዎች ተበራክተዋል ያለው ፓርቲው እንዲህ ያለው ተጽዕኖ ካረፈባቸው በዓላት ውስጥ የጥምቀት ክብረ በዓል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው ብሏል። ይህንኑም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት "የጥምቀት በዓል አከባበርን እና ወቅታዊ ጉዳዮችን" መሠረት አድርጎ ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከተሰጠው መግለጫ ፓርቲያችን ለመረዳት ችሏል ብሏል በመግለጫው። በዓሉ የአለም ቅርስ እንደመሆኑ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በክብረ በዓሉ የሚሳተፉ ምዕመናንና ጎብኚዎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ ለበዓሉ ስኬታማነት…
