ሀገርኛ

“በማንኛውም ጊዜ የፀጥታ ችግር ቢከሰት ሃላፊነቱን አልወስድም ” ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ

“በማንኛውም ጊዜ የፀጥታ ችግር ቢከሰት ሃላፊነቱን አልወስድም ” ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ

15/05/16 በተለያዩ ጊዜያት በፋኖ እና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል ውግያ የተካሄደባት የደብረ ብርሃን ከተማ በአሁኑ ወቅት አንፃራዊ ሰላም በአከባቢዉ ቢስተዋልም ባለው ነባራዊ ሁኔታ አስጊ የሆነ የፀጥታ ችግሮች አሁንም በስጋትነት ያሉ በመሆኑ በማንኛውም ወቅት የፀጥታ ችግር ቢከሰት ሃላፊነቱን እንደማይወስድ የደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ አስታወቀ ፡፡ ነባር ተማሪዎች እና አዳዲስ ተማሪዎች ከጥር 23ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እንዲገቡ ጥሪ ያደረገው ዩኒቨርስቲው ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ቢፈጠር ሃላፊነቱን እንደማይወስድ አሳውቋል። የ2016ዓ.ም የመማር የማስተማር ሂደት በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የተስተጓጎለ መሆኑን የሚገልጹት የዩኒቨርሲቲው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሞሃመድ መስከረም ወር መጨረሻ 2016ዓ.ም የጤና ተማሪዎችን እና የ2016ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን እንዲሁም ጥቅምት መጨረሻ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በኦሮሚያ ክልል “በመርዛማ ጋዝ” በብልጽግና ፓርቲ ሠራዊት ጥቃት እየተፈጸመ ነው- ኦነግ

በኦሮሚያ ክልል “በመርዛማ ጋዝ” በብልጽግና ፓርቲ ሠራዊት ጥቃት እየተፈጸመ ነው- ኦነግ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ኦነግ ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ  “የብልጽግና ፓርቲ ወታደራዊ ሃይል” ሲል የጠራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል ድሮን በመጠቀም በንጹሃን ዜጎች ላይ  ወንጀል   እየፈጸመ ነው አለ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር  ኦነግ  ባለፈው እሁድ ጥር 12 ቀን 2016 በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ ጊቢሶ ቀበሌ “የድሮን አውሮፕላኖች የመርዝ ጋዝን በመጠቀም” በሠላማዊ ሰዎች ሰፈሮች ላይ የመንግስት ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የሠላማዊ ዜጎች ንብረት ወድሟል። ይህን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎችም ጥር 12 እና 13 ቀን 2016 ማለትም እሁድና ሰኞ በተፈጸሙ ጥቃቶች ፓርቲው በስም የጠቀሳቸው አምስት ሰዎችን ጨምሮ “በርካታ ንጹሐን ዜጎች” ሲሞቱ ቁጥራቸው ያልተጠቀሰ…
ተጨማሪ ያንብቡ
 በትግራይክልል  28% ህፃናት የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

 በትግራይክልል  28% ህፃናት የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

አሸናፊ አሰበ 14/06/2016 በትግራይ ክልል ከተከሰተው አስከፊ ድርቅ ጋር ተያይዞ   ህፃናት በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጥረት እየተጎዱ ነው የክልሉ ጤና ቢሮ ከ ትግራይ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጋር በመተባበር በጋራ አካሄድኩት ባላው ጥናት 26% የክልሉ ህጻናት መካከለኛ እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው መረጋገጡን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የ ስነ-አመጋገብ ጉዳይ ቡድን አስተባባሪ አቶ መንገሻ ባህረሥላሴ ለ አዲስ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ እንደ ሃላፊው ገለጻ ጥናቱ የተካሄደው በትግራይ ክልል ውስጥ ካሉ ወረዳዎች ውስጥ በ 36 ቱ ብቻ ሲሆን በምግብ እጥረት ምክንያት በሆስፒታሎች ውስጥ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንም አክለዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሚያስተዳድራቸው 73 ወረዳዎች ውስጥ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የሚገኘው ድጋፍ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ አደጋ አጋጠመው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ አደጋ አጋጠመው

09/05/2016 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን፤ ዛሬ ሐሙስ በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራትቶ መውጣቱን  ሆኖም በአደጋው በመንገደኞችም ላይ ሆነ የበረራ ሰራተኞች  ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ  አየር መንገዱ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአውሮፕላኑ ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡ ጉዳት የደረሰበት የአየር መንገዱ አውሮፕላን  የበረራ ቁጥር ኢቲ 106 ሲሆን ፤ ከአዲስ አበባ የተነሳው ከቀኑ 6፡30 እደሆነ ታውቋል። ክስተቱ የደረሰው ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከአስ8፡10  ደቂቃ ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል። አየር መንገዱ  ለተፈጠረው ችግር ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቆ “የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ” ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡

09/05/2016 የአረብ ሊግ በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልፅ የጣሰ ነው፤  ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚፃረር ነው በሚል ተቃውሟል። የአረብ አፍሪካና የዓለም አቀፍ መርሆች ላይ በግልፅ የተሰነዘረ ጥቃት ነውም ብሏል። የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሊጉ መግለጫ፥ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለውታል፡፡ አክለው  ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት ሆኖም የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ ነው ብለዋል፡፡ የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ ባካሄደው የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ በኢትዮጵያና…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ስብሰባ ጠራ 

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ስብሰባ ጠራ 

ጥር 08/2016 በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሊመክር እንደሆነ በአፍሪካ ህብረት እና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናት እና ምርምር የሚያደርገው “አማኒ አፍሪካ”    አስነብቧል፡፡በስብሰባው ላይ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማብራሪያ እንደሚያቀርቡ  ይጠበቃል፡፡ ስብሰባውን በንግግር የሚከፍቱት የዚህ ወር የምክር ቤቱ ሊቀመንበር የሆኑት፤ በአፍሪካ ህብረት የጋና አምባሳደር አማ ቱም-አሙሃ ናቸው።  እርሳቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴዎዬ፤ ጉዳዩን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ገለጻ እንደሚሰጡ “አማኒ አፍሪካ” አስታውቋል። በአፍሪካ ግጭቶችን የመከላከል እና ከተከሰቱም በኋላ የመቆጣጠርና መፍትሄ የማበጀት ዓላማ ያለው የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት 15 አባል…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ ለቀቀች

ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ ለቀቀች

ሱዳን፣ ኢጋድ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብቷል በማለት ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ዛሬ አስታውቃለች። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆነችው ጅቡቲ አቻቸው በጻፉት ደብዳቤ፣ ይህንኑ ውሳኔ አሳውቀዋል። ሱዳን ከኢጋድ ጋር ግንኙነቷን ያቋረጠችው፣ በመጭው ሐሙስ ኡጋንዳ ላይ የተጠራው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባዔ ወታደራዊውን መንግሥት ሳያማክር የሱዳኑን ጦርነት አጀንዳው ማድረጉንና የፈጥኖ ደራሹን ኃይል እንዲገኙ መጋበዛቸውን በመቃወም ነው። የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በኢጋድ ጉባኤ ላይ እንደማይገኙ ከትናንት ወዲያ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢጋድ አስቸኳዩን የመሪዎች ጉባኤ የጠራው፣ በሱዳኑ ጦርነት ዙሪያ ለመወያየትና የኢትዮጵያና ሱማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትን ለማብረድ ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ
ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሊሆን ነው

ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሊሆን ነው

ኢትዮጵያዊያን የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት የዲጂታል መታወቂያን ግዴታ ወደ መሆን ሊሸጋገር እንደደሆነ  የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ዳይሬክተር ዮዳሔ ዘሚካኤል ተናግረዋል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኩል በተለያዩ ምዕራፎች ይተገበራል ከተባለው የምዘገባ ሂደት በኋላ  ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት እንደሚታገዱ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡  ዳይሬክተሩ፣ ተቋማት ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ደንበኞቻቸውን አገልግሎት የመንፈግ ሕጋዊ መብት አላቸው ማለታቸውም ተገልጧል። እስከ አሁን አገልግሎቱን ለማግኘት አራት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል፡፡ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 መታወቂያ ለማግኘት ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸውን ሁሉንም ዜጎች ለመመዝገብ ተይዞ የነበረው ቀነ-ገደብ ወደ 2028  ተሸጋግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
በእናቶችና አረጋውያን ሴቶች ላይ ግርዛት እየተፈጸመ ነው፡፡

በእናቶችና አረጋውያን ሴቶች ላይ ግርዛት እየተፈጸመ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን በሻሸጎ ፣ ሶሮና ምዕራብ ሶሮ ወረዳዎች በሴቶች ላይ በሚፈጸም ግርዛት ዙሪያ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶችን ይፋ አድርጓል። በሻሸጎ ወረዳ በማኅበረሰቡ ዘንድ ‘ጨበላ’ በመባል የሚታወቅ የተደጋጋሚ ግርዛት ጎጂ ልማድ በአካባቢው በበጋ ወራት በሁሉም ዕድሜ ክልል በሚገኙ ሴቶች ላይ በስፋት እንደሚፈጸም እንዲሁም ሴቶችና ሴት ሕፃናት መራቢያ አካላቸው አካባቢ ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እንደመፍትሔ የሚወሰድ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ጎጂ ልማድ የሚያልፉ ሴቶች ከጤና እክል ጀምሮ እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት የሚደርስባቸው መሆኑ በክትትሉ ከተለዩ ግኝቶቹ መካከል መሆኑን ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ተጎጂዎች ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እየተሰጠ ያለው ድጋፍና ክትትል አጥጋቢ አለመሆን ሴቶች…
ተጨማሪ ያንብቡ
አሜሪካ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማፅዳት የምታደርገውን ዘመቻ እደግፋለሁ አለች::

አሜሪካ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማፅዳት የምታደርገውን ዘመቻ እደግፋለሁ አለች::

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ የአሜሪካ መከላከያ ኃይልና የኢምባሲው የጸጥታ ትብብር ቢሮ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማጽዳት እያደረገች ያለውን ዘመቻ ለማገዝ ከኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ተቋም ጋር የጋራ ፕሮጀክት መጀመራቸውን  አስታውቋል። ኢምባሲው፣ ኢትዮጵያ ፈንጂዎችን ለማጽዳት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ፣ ፔንታጎን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በትብብር የሚሠሩ ባለሙያዎችን መላኩን ገልጧል።የቡድኑ አባላት ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰብዓዊ ፈንጂ ማምከን ማሰልጠኛ ማዕከል እና ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጦር መሳሪያ ማስወገድ እና ቅነሳ ፕሮግራም የተውጣጡ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ  ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የዳሰሳ ጥናቱን እና ቀጣይ ድጋፎችን በተመለከተም  የኤምባሲው ተወካዮች እና የባለሙያዎች ቡድኑ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊዎች ጋር   ጥር 6፤ 2016…
ተጨማሪ ያንብቡ