ኢትዮጵያዊያን የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት የዲጂታል መታወቂያን ግዴታ ወደ መሆን ሊሸጋገር እንደደሆነ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ዳይሬክተር ዮዳሔ ዘሚካኤል ተናግረዋል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኩል በተለያዩ ምዕራፎች ይተገበራል ከተባለው የምዘገባ ሂደት በኋላ ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት እንደሚታገዱ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ፣ ተቋማት ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ደንበኞቻቸውን አገልግሎት የመንፈግ ሕጋዊ መብት አላቸው ማለታቸውም ተገልጧል። እስከ አሁን አገልግሎቱን ለማግኘት አራት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል፡፡ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 መታወቂያ ለማግኘት ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸውን ሁሉንም ዜጎች ለመመዝገብ ተይዞ የነበረው ቀነ-ገደብ ወደ 2028 ተሸጋግሯል፡፡
