ሀገርኛ

ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ያላትን ልዩነት መፍታት እንዳልቻለች ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ያላትን ልዩነት መፍታት እንዳልቻለች ተገለጸ

በዋሸንግተን በሚካሄደው የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ እየተካፈለች ትገኛለች፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት የጠየቀች ሲሆን ተቋሙ ግን ብድር ለኢትዮጵያ ከመስጠቱ በፊት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡ከተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ኢትዮጵያ የብሯን የመግዛት አቅም እንድታዳክም የሚለው ሲሆን ይህ ጉዳይ እስካሁን አጨቃጫቂ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት ድርድር ሲያደርጉ ከአንድ ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን በየጊዜው ሳይስማሙ በመለያየት ላይ ናቸው፡፡ከአንድ ወር በፊት የዓለም ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለ15…
ተጨማሪ ያንብቡ
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን ቢቢሲ በምርመራ ማረጋገጡን ዘግቧል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን ቢቢሲ በምርመራ ማረጋገጡን ዘግቧል፡፡

በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ  በምርመራ ማረጋገጡን ዘግቧል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አመራሮችም በፓርቲው የወረዳ መዋቅሮች ትዕዛዝ በተለይም የመንግሥትን ገፅታ በሰው ሰራሽ መንገድ ለመገንባት ፌስቡክ ላይ በሚደረጉ አሳሳች ዘመቻዎች ላይ እንደሚሳተፉም ተናግሯል፡፡ ቢቢሲ ለዚህ ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ አመራር፣ የፓርቲ አባል እንዲሁም በከተማዋ እና በፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች  አነጋግሬያለሁ ያለ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የፖለቲካ ውጥረት በተፈጠረ ቁጥር ጋዜጠኞችን ማሠር እንዲያቆሙ  ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ድርጅቱ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጸጥታ ኃይሎች ስምንት ጋዜጠኞችን እንዳሠሩ ገልጦ፣ እስር ቤት በሚገኙ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ ደሞ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ብሏል። የበይነ መረብ ጋዜጠኞቹ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና ከሁለት ወራት በፊት የታሠረው የሱማሌ ክልሉ ጋዜጠኛ ሙሂያዲን ሞሃመድ ባስቸኳይ እንዲፈቱና በገነት ላይ ተፈጽሟል የተባለው ጥቃትም እንዲጣራ ሲፒጄ ጠይቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የራያ አለላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ

የራያ አለላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ

ከተማዋ በመከላከያ እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ወድቃለች እታገኘሁ መኮነን የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሃይሉ አበራ ተናግረዋል፡፡ ከተማዋም ከሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም. ጀምሮ  በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መግባቷ ተሰምቷል፡፡ አቶ ሃይሉ የአቶ ሞላ ህልፈትከትግራይ ኃይሎች ጋር በተደረገ “ውጊያ” አይደለም ብለዋል፡፡ በህግ የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ ምክንያቱን ለመግለጽ ፍቃደኛ አይደለሁም ብለዋል፡፡ የከተማዋ  ነዋሪዎች ከሰኞ ከሰዓት ጀምሮ በርካታ ነዋሪዎች ከተማውን ለቀው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሄዳቸውን ተናግረዋል። አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ወደ ቆቦ ከተማ መግባታቸውም ተሰምቷል፡፡ የራያ አላማጣ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “የአማራ ታጣቂዎች” ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል ተናገረ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “የአማራ ታጣቂዎች” ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል ተናገረ

በአማራ ታጣቂዎች የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ ታደሰ ወረደ ተናገሩ። አቶ ታደሰ  “የመጀመሪያው እርምጃ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችን ማፍረስ እና የተቋቋሙትን ህገ-መንግስታዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ማፍረስ ሲሆን "የፍትህ ስርዓቱን ወደነበረበት መመለስ" በተከታይነት ይሰራል ብለዋል። ጄኔራሉ የታጠቁ ሃይሎች ከፌዴራል ሃይሎች ጋር መጠነኛ ግጭት በመፍጠር ሂደቱን እያስተጓጎሉ መሆናቸውንም አብራርተው የፕሪቶሪያ ስምምነት ግጭት እንዳያገረሽ በሚከላከል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ እንደገለጹት የፕሪቶሪያ ስምምነት የግዛትን ጨምሮ ሁሉም አለመግባባቶች በህገ መንግስቱ መሰረት መፈታት እንዳለባቸው መደንገጉን አስታውሰዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ግን ትናንት  በማህበራዊ ትስስር…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ

የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ

አንድ የኢትዮጵያ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ቻይናዊ ሯጭ የቤይጂንግ ግማሽ ማራቶንን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ተጀመረባቸው። የውድድሩ አዘጋጅ ቤይጂንግ ስፖርትስ ቢሮ ክስተቱን እየመረመርኩ ነው ሲል ለፈረንሳይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ተናግሯል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ቢቂላ እንዲሁም ኬንያውያኑ ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ማናንጋት ቻይናዊው አትሌት ሂ ጂ እንዲያሸንፍ ያደረጉበት ሁኔታን የተመለከቱ ቻይናውያን “ስፖርታዊ ሥነ ምግባር የሌለበት አሳፋሪ ተግባር” ሲሉ ገልጸውታል። ሦስቱ አትሌቶች ከውድድሩ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ ቻይናዊውያን አትሌት አጅበው ሲሮጡ ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት በተጋራው ቪዲዮ ላይ የውድድሩ መጨረሻ አካባቢ ሦስቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናዊው አትሌት እንዲያልፋቸው በእጃቸው ሲጠቁሙት ይታያሉ። በመጨረሻም…
ተጨማሪ ያንብቡ
በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው የራያ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ ወረዳ “የህወሓት ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት” ከቅዳሜ እስከ ዛሬ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ሲናገሩ፣ የደቡባዊ ትግራይ ዞን በበኩሉ ግጭት የተፈጠረው ታጣቂዎች በትግራይ ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈታቸው መሆኑን ገልጿል። ከየካቲት ወር ጀምሮ በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገባቸው ካሉት የራያ ወረዳዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ የተከስ ልውውጡ በድጋሚ ያገረሸው ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው እና የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ “የህወሓት ኃይሎች” በማለት የሚጠሯቸው ታጣቂዎች፤ ተኩስ የከፈቱት በወረዳው አዲስ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን “አሳፋሪ” የምርመራ ሂደት እየተከተለ ነው – ኦነግ 

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን “አሳፋሪ” የምርመራ ሂደት እየተከተለ ነው – ኦነግ 

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባወጣው መግለጫ የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት በቴ ኡርጌሳ ግድያን በተመለከተ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን “አሳፋሪ” የምርመራ ሂደት እየተከተለ ነው ሲል ተናገረ ።  ኦነግ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ፤ ግንባሩ በመንግስት በኩል የሚደረገው “ምርመራ ተዓማነት የጎደለው ፣ የማስረጃ ችግር እና ሀሰተኛ ማስረጃዎችም የቀረቡበት ነው ሲል ተችቷል፡፡ ስለዚህም በባቲ ኡርጌሳ ግድያ ላይ የሚደረገው ምርመራ እየተባለ የሚጠራው መረጃ ከጅምሩ ሆን ተብሎ በተዘበራረቁ በርካታ ማስረጃዎች፣ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የሀሰት ዘመቻዎች የተበላሸ መሆኑን ደግመን እንገልፃለን። ሁኔታው በደርግ ጊዜ የነበረውን  የቀይ ሽብር ወቅትን ይመስላሉ ሲል ኦነግ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም በቴ ኡርጌሳ ከእንግዳ ማረፊያው ሲወሰድ የተመለከቱ አንድ የጥበቃ ሰራተኛ ከክስተቱ…
ተጨማሪ ያንብቡ
አዳማ ከተማ የ9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አሸኛፊ ሁና ተመረጠች::

አዳማ ከተማ የ9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አሸኛፊ ሁና ተመረጠች::

 የካቲት 15/2016 ዘንድሮ የዘጠነኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ተረኛ አዘጋጅ  የወላይታ ሶዶ ከተማ ነበረች፡፡ፎረሙን የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ፣ የኢፌዲሪ ከተማና መሰረተ ልማት ሚስቴርና የወላይታ ሶዶ ከተማ አሰተዳደር በጋራ አሰናድተውታል፡፡ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቆየው በዚህ ዓውደ ርዕይ ላይ 124 ከተሞች በከተማ ልማት ዘርፍ ያከናወኗቸውን ተግባራት ለጎብኝዎች አስተዋውቀዋል፡፡ዓውደ ርዕዩ ከተሞች ልምድ የተለዋወጡበት፣ ሃሳባቸውን ያጋሩበት፣ የዕውቀት ሽግግር ያደረጉበት  መድረክ ነበር፡፡ “የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር  አቶ ተመስገን ጥሩነህ አማካኝነት ተከፍቶ ለአንድ  ሣምንት ቆይታ አድርጎ ተጠናቋል፡፡ ከተሞች ካቀረቡት ዓውደ ርዕይ ጎን ለጎን በከተማ ልማት ዘርፍ በተለያዩ ጽንሰ ሃሳቦች ዙሪያ  የፓናል ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ህወሓት ኬሪያ ኢብራሂም እና ሙሉ ገብረ እግዚብሔርን ከፓርቲ አባልነታቸው አሰናበተ

ህወሓት ኬሪያ ኢብራሂም እና ሙሉ ገብረ እግዚብሔርን ከፓርቲ አባልነታቸው አሰናበተ

የካቲት 15/2016 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ትላንት ሐሙስ የካቲት 15፤ 2016 ባደረገው ስብሰባ ከከፍተኛ አመራሮቹ ውስጥ፤ ኬሪያ ኢብራሂም እና ሙሉ ገብረ እግዚብሔርን ከማዕከላዊ ኮሚቴ እና ከፓርቲ አባልነታቸው ማሰናበቱን አስታወቀ። ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ እና ዶ/ር አብርሃ ተከስተ በፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡ ህወሓት በጦርነቱ ወቅት “በጠላት እጅ ወድቀው ነበር” ያላቸውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን  ያሰናበተው አስቀድሞ የነበሩትን ሁኔታዎች በመገምገም እና የፓርቲውን ህገ ደንብ በመከተል መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በዚህም መሰረት “እጃቸውን ለጠላት በመስጠት” እና “ምስጢር አሳልፈው በመስጠት” የተገመገሙት የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉ ገብረ እግዚብሔር፤ ከማዕከላዊ…
ተጨማሪ ያንብቡ