የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የፖለቲካ ውጥረት በተፈጠረ ቁጥር ጋዜጠኞችን ማሠር እንዲያቆሙ  ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ድርጅቱ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጸጥታ ኃይሎች ስምንት ጋዜጠኞችን እንዳሠሩ ገልጦ፣ እስር ቤት በሚገኙ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ ደሞ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ብሏል። የበይነ መረብ ጋዜጠኞቹ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና ከሁለት ወራት በፊት የታሠረው የሱማሌ ክልሉ ጋዜጠኛ ሙሂያዲን ሞሃመድ ባስቸኳይ እንዲፈቱና በገነት ላይ ተፈጽሟል የተባለው ጥቃትም እንዲጣራ ሲፒጄ ጠይቋል።