ሐቅን ፍለጋ
መረጃ የምናገኝበት አማራጭ አድጓል፡፡የምናገኛቸው መረጃዎች በሙሉ ግን የተጣሩ እና ትክክለኛ መሆናቸውን የማረጋገጥ ልማዳችን ግን ገና ነው፡፡የጋዜጠኛ ሥራ መሰረቱ እውነታን በማጣራት እና በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ተሰራጭተው የምናገኛቸው መረጃዎች ሁሉ ግን በጋዜጠኞች እና ኃላፊነት በሚሰማቸው መገናኛ ብዙሃን የተዘጋጁ አይደሉም። አሁን ኢትዮጵያን ከሚፈትኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ነው፡፡በተለያዩ ጊዜዎች የተከሰቱ ግጭቶችን እና ወቅታዊ ጉዳዮችን ተከትሎ ደግሞ እነዚህ የመረጃ መዛባቶች እና ሀሰተኛ መረጃዎች ይበራከታሉ፡፡ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ ለማድረግ ስትዘጋጅ አንደኛው ስጋቷ የነበረው ይሀው ጉዳይ ነበር።የምርጫ ወቅቶች የሚኖሩ መረጃዎች የመራጮች ውሳኔ ላይ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተፅእኖ ይኖራቸዋል፡፡ አዲስ ጊዜ ሐቅ ለማጣራት የእውነት ማጣሪያ አምድን በድረገጹ አዘጋጅቷል፡፡ይህ የእውነት ማጣሪያ…
