ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።
ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ባንኩ በአፍሪካ ትልቁን ያልተነካ ገበያ እየፈለገ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሁለት ሳምንት በኃላ ከውጭ የፋይናንስ ተቋማት የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ ማመልከቻዎችን እንደሚቀበል በመግለፁ ጥሪውን ተቀብሎ ፍቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት ዝቅተኛው የተከፈለ ካፒታል ለዉጪ ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር እና ከባንክ ላልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት 25 ሚሊዮን ብር ሀብት ሊኖራቸው ይገባል። ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በባንክ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የውጭ ባለሀብቶች የባንክ ፈቃድ ለመስጠት ማቀዷን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ በኢትዮጵያ…